tgoop.com/youthkiper/11729
Last Update:
🌿ከ Life ብዙ ተምሬያለሁ!
⚜️. አንዳንድ ሰው እንዲያፈቅራችሁ ማድረግ እንደማይቻል ተምሬያለሁ ፤ ማድረግ የሚቻለው ጥሩ አፍቃሪ መሆን ብቻ ነው ።
⚜️.ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን ተሞክሮዎች ዓይነትና ከተሞክሮዎቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጅ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምሬያለሁ ።
⚜️.እንዳንዴ የቱንም ያህል ለሌሎች ብጨነቅ እና ግድ ብሰጥ አንዳንዴ አንዳንዶች በመልሱ ግድ ላይሰጡ እንደሚችሉ ተምሬያለሁ ።
⚜️.ቤተሰብ ሁልጊዜም መከታ ድጋፍ እንደማይሆን ተምሬያለሁ ። ጓደኞች ምንም ያህል ጥሩ ቢሆን አልፎ አልፎ ማስቀየማቸው እንደማይቀር ተምሬያለሁ ። ባስቀየምናቸው ሰዎች ይቅር መባል በቂ ያለመሆኑንና ራስንም ይቅር ማለትም እንደሚያስፈልግ ተምርያለሁ ።
⚜️.መታመንን ለመግንባት ዘመናት እንደሚያስፈልግ ፤ ለማውደም ግን ሰከንዶች ብቻ እንደሚበቁ ተምሬያለሁ ።
⚜️.አንዳንድ ጊዜ ተንሸራትተህ ስትወድቅ ይረጋግጡኛል ብለህ የምትጠብቃቸውና የምትፈራቸው ሰዎች ብድግ አድርግው በማንሳት እንደሚያስገርሙህ ተምሬያለሁ ።
⚜️.እውነተኛ ጓደኝነት እንደዚህም እውነተኛ ፍቅር በቦታ ርቀት ሳይግደብ ማበብ መፍካቱ እንደማይቆም ተምሬያለሁ ።
⚜️.በአስተዋይነት "እምቢ" ማለት ሁልጊዜም የንፉግነት ምልክት ያለመሆኑን “እሺ” ማለትም ሁልጊዜ ምግባረ ሰናይነትን እንደማያሳይ ተገንዝቢያለሁ ።
⚜️.ራስን ከጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ከጥላቻ የምንገላገልበት ብቸኛ መንገድም የአለፈውን ጊዜ ረስተን ከአሁን ጋር እርቅ ማድረግ ስንጀምር እንደሆነ ተምርያለው ።
📚የአልኬሚስት
ደራሲ ፖውሎ ኩዌልሆ
ነገ መልካም ይሆናል !
BY ወጣቱ ና ሙዱ
Share with your friend now:
tgoop.com/youthkiper/11729