tgoop.com/ytewahido_lijoch/475
Create:
Last Update:
Last Update:
ኤልያስን እግዚአብሔር ጠዋትና ማታ የመገበው በቁራዎች ነበረ::
በጣም ይገርማል ቁራን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የምናውቀው ኖኅ ልኮት ቀልጦ ሲቀር ነበር:: እስከዛሬም የቁራ መልእክተኛ ብለን እንተርታለን::
ቁራ ልጆቹን እንኩዋን የማይመግብ እንደነበረ መዝሙረ ዳዊትም ይናገራል:: ብቻ ቁራ ሆዳም በአጭሩ የሚበርር ጅብ ነገር ነው:: እግዚአብሔር አዝዞት ግን የኤልያስ አስተናጋጅ ሆኖ ሰዓት ጠብቆ እየመጣ ሦስት ዓመት ሙሉ መገበው::
ጌታ ሲያዝዘው የማይታዘዝ የለም:: ንፉጎቹን ላንተ ሲል ቸር ማድረግ ይችላል:: ከበላተኛው መብል ይሠጥሃል:: ቀጠሮ የማያከብሩትን ለአንተ ግን አክብረው እንዲመጡ ሊያደርግልህ ይችላል::
የኤልያስ አምላክ ወዴት ነህ? ብለህ ለምነው!
ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot
ለመቀላቀል ...👇
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
BY የተዋህዶ ልጆች ❤️
Share with your friend now:
tgoop.com/ytewahido_lijoch/475