Telegram Web
Forwarded from 📚 Biranaye Tube 📖 (Biranaye tube)
የከንቲባው ልጅ መፅሐፍ website ላይ መነበብ ጀምሯል ...👇👇👇
https://www.ethiobookreview.com/book/yekentibaw-lej-biranaye
Forwarded from 📚 Biranaye Tube 📖 (Tesfa)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2.5 ሚሊዮን ዶላር 🥸❤️👏🙏

ኮሜዲያን እሸቱ በኳታር እየተገነባ ባለው ለቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን

በዩቱብ ቀን ና ለሊት live በመግባት በ15 ቀን ውስጥ 2.5 ሚልዮን ዶላር አስባስቧል::

እሱም 6ሺህ ዶላር ለቤተክርስቲያኗ ማሰሪያ
በራሱ በባለቤቱ ና በልጅ ስም ገቢ አድርጏል::

2.5 ሚሊዮን ዶላር 🥸❤️👏

Join us...
    ✦✺ @Biranayetube ✺✦
    ✦✺ @Biranayetube ✺✦
Forwarded from 📚 Biranaye Tube 📖 (Tesfa)
የብርብር ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ማህበረ ካህናት እንዳልካቸው ዘነበን ከቅድስት ቤተክርስትያን እንዲታገድ ምክንያት የሆኑ ህጸጻዊ የእምነት ልምምድ።

በቲክ ቶክ live ውይይት ላይ ከተናገረው

1ኛ
"ትርኪምርኪ ነገር ላይ ጊዜዬን ማሳለፍ አልፈልግም፣በህይወት እያሉ ቅዱሳን ያማልዳሉ አያማልዱም አልልም። ሴጣን ነው የሰጠኝ አጀንዳ። በጥቃቅን ነገር ላይ ጊዜዬን አላባክንም።"

የመልእክቱ አንድምታ

ቅድስት ቤተክርስቲያን ስለቅዱሳን የህይወት ግብራቸው፣ገድላቸው እና ቅድስናቸውን ነገረ ቅዱሳን፣ክብረ ቅዱሳን እያለች ርዕስ ሰጥታ እንደምታስተምር እና መሰረታዊ ከሆኑ የነገረ ሃይማኖት ትምህርቶች መሃል አንዱ እንደሆነ እየታወቀ ነገረ ቅዱሳንን የሴጣን አጀንዳ የሚል የድምዳሜ መልእክት ማስቀመጡ።

2ኛ
"ስለ ማህበር ፣ስለጽዋ፣ስለእንትን እያወራን እኮ ኢየሱስን ጋረድነው።"

የመልእክቱ አንድምታ

ስርዓተ ዝክር እና ጽዋን የኢየሱስ ክርስቶስ መሸፈኛ የስህተት መንገድ አድርጎ የማሳዬት ዝንባሌ ፈጽሟል።

3ኛ
"የሆነ ሰው መጥቶ መስቀል ምናምን ቢለኝ አላወራም። ደከመኝ በቃኝ።"

የመልእክቱ አንድምታ

ነገረ መስቀሉ አድካሚ አሰልች እንጅ ለነገረ ድህነት ምንም ጥቅም የሌለው ትርፍ ስርዓት እንደሆነ በንግግሩ በመግለጥ

4ኛ
"ታቦት ላይ የዘለዓለም ህይወት የለም፣መስቀል ላይ የዘለዓለም ህይወት የለም።"

የመልእክቱ አንድምታ

የታቦተ ህግ ስርዓት፣ነገረ መስቀሉ በክርስትና ውስጥ የማይጠቅም እንደሆነ በማሳዬት

5ኛ
"ከፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ጋር የምንግባባት አንድ ነገር አለ "እሱም ኢየሱስ ነው"

የመልእክቱ አንድምታ

ቅድስት ቤተክርስቲያን በውግዘት ከተለያዬች አብያተክርስቲያናት ጋር የምትጋራው አምላክ እንዳላት በማሳዬት

እዚህ ውስጥ ኢየሱስ ስለጠራ እንዳልካቸው ዘነበ ታገደ የሚል አንድም አንቀጽ የለውም።
Forwarded from Tesfa
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡ እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር ፣ አህያ ጌታዋን ስትመክር ፣ ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ ፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን ፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር ፣ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ ፣ የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ ፣ የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል ፣ የሙሴ በትር እባብ ሲሆን ፣ ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር ፣ የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ ፣ የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ ፣ የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ?

ሔዋን ከእባብ ጋር ተነጋገረች የሚለውን አምነህ አቡነ አረጋዊ በእባብ ተራራ ወጡ ሲባል ከቀለድህ ፣ ኤልያስን ቁራ መገበው ሲባል ተቀብለህ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቁራውን መገቡት ሲባል ከዘበትህ ፣ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር አደረ ሲባል አምነህ አቡዬ አንበሶች ጋር ነበሩ ሲባል ካጣጣልክ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ያለቀበት ቀን ለአንተ የዓለም ፍጻሜ መስሎሃል ማለት ነው::

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
  ✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
  ✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
Forwarded from Tesfa
ኤልያስን እግዚአብሔር ጠዋትና ማታ የመገበው በቁራዎች ነበረ::

በጣም ይገርማል ቁራን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የምናውቀው ኖኅ ልኮት ቀልጦ ሲቀር ነበር:: እስከዛሬም የቁራ መልእክተኛ ብለን እንተርታለን::

ቁራ ልጆቹን እንኩዋን የማይመግብ እንደነበረ መዝሙረ ዳዊትም ይናገራል:: ብቻ ቁራ ሆዳም በአጭሩ የሚበርር ጅብ ነገር ነው:: እግዚአብሔር አዝዞት ግን የኤልያስ አስተናጋጅ ሆኖ ሰዓት ጠብቆ እየመጣ ሦስት ዓመት ሙሉ መገበው::

ጌታ ሲያዝዘው የማይታዘዝ የለም:: ንፉጎቹን ላንተ ሲል ቸር ማድረግ ይችላል:: ከበላተኛው መብል ይሠጥሃል:: ቀጠሮ የማያከብሩትን ለአንተ ግን አክብረው እንዲመጡ ሊያደርግልህ ይችላል::

የኤልያስ አምላክ ወዴት ነህ? ብለህ ለምነው!

ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot

ለመቀላቀል ...👇
  ✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
  ✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
Forwarded from Tesfa
ዓለም የተደነቀበት አስገራሚ ተዓምር - ቅዱስ ሚካኤል ለጴንጤዋ ተገልጦ ከሞት በማዳን ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ...👇👇👇
https://youtube.com/watch?v=QmjXs5PnR5M&si=joEX9dX8tFwAl7b-
Forwarded from 📚 Biranaye Tube 📖 (Tesfa)
ማዕዶት ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም አዳራሽ ታሪክ ተሰራ - maedot le Ethiopia...👇👇👇
https://youtube.com/watch?v=7u3e0yhu27M&si=tZI7BMZYqg9pkZye
Forwarded from 📚 Biranaye Tube 📖 (Tesfa)
#ዜና #መረጃ #ሀዘን

ጎፋ ዞን በተከሰተው አደጋ ውድ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎቻችን እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ያሳርፍ።

በዚህ አደጋ መራር ሀዘን የደረሰባችሁ ሁሉ ፈጣሪ ያፅናችሁ።

Join us...
    ✦✺ @Biranayetube ✺✦
    ✦✺ @Biranayetube ✺✦
Forwarded from Tesfa
የምራቸውን ነው 'ሐዋዝ ወደ ቤተክርስቲያን የተመለሰው ነውር ሠርቶ ነው' የሚሉት?

መቼም ነውር ሠርቶ ለመሸሸግና ጻድቅ ጻድቅ ለመጫወት የት ይቀላል አልልም። ግን "ታድሰናል። በጸጋው ድነናል። ንስሀና ሥራ አያስፈልገንም።" እያሉ፣ እነሱ ጋ የነበረን ሰው ነውር መቁጠር እንዴት ቻሉበት? "በጌታ" ነኝ ምንም ብሠራ ደሙ አድኖኛል፣ ካሉ ወዲህ ነውር ጌጥ መሆኑም አይደል? ያም ይቅር ቤተክርስቲያን የነፍስ ሆስፒታል ናት። የጻድቃን ጉባዔ ሳይሆን፣ የመጽደቅ ተስፋ ያላቸው፣ እንደቸርነትህ ማረን የሚሉ ምዕመናን ያሉበት ስብስብ ነው።

የእውነት ካሳሰባችሁና እግዚአብሔርን ከፈራችሁ፣ ቢያንስ ስለ ወንድማችሁ ደስታ እና የአእምሮ ሰላም ደስ ይበላችሁ። ግድ ተያይዘን እንጥፋ አለ እንዴ? ደግሞ ምናለ ወደራስ ማየት ቢቻል? እሱ አንድ ጊዜም ተገፍቼ ወጣሁ አለለም። እዚያ ስላሉትም ሲያወራ የወዳጅነት ፍቅር እና ናፍቆት እንዳለው፣ ግን ነፍሱን ማዳን ስላለበት የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዳስበለጠ ነው። በዚህ ልክ ለምን ይረብሻቸዋል?

"በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን፥ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።" ~ ማቴዎስ ፯: ፬-፭

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
2025/01/16 07:19:10
Back to Top
HTML Embed Code: