tgoop.com/Abulabas/2247
Last Update:
ክፉ ልክፍት!... ድንቅ መድሃኒት!
~
* ሰውየው፡ “ቀድሞ (ለማጨት ሳስባት) በሚስቴ በምደነቅ ጊዜ … አላህ የሷ አይነት በዓለም ላይ የፈጠረ አይመስለኝም ነበር። ካጨኋት በኋላ ብዙዎቹ ሴቶች የሷው አምሳያ ሆነው አገኘሁ። ካገባኋት በኋላ #ብዙዎቹ ሴቶች ከሷ የበለጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ተገነዘብኩ። ተጋብተን ጥቂት አመታት ካለፉ በኋላ ግን #ሁሉም ሴቶች ከሷ የሚበልጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ደመደምኩ” አለ።
- ሸይኹ በዚህን ጊዜ፡- “ይልቅ ከዚህ የከፋውን አልነግርህም?” አሉት።
* “ይንገሩኝ” አለ ሰውየው።
- “የዓለም ሴቶችን በሙሉ ብታገባም በየጎዳናው የሚልከሰከሱ ውሾች ከአለም ሴቶች ሁሉ በላይ ቆንጆዎች ይሆኑብሃል!” አሉት።
* ሰውየው፡- በስሱ ፈገግ አለና “ለምን እንዲህ አሉ?” ሲል ጠየቃቸው።
- ሸይኹ፡- “ምክንያቱም ችግሩ ከሚስትህ አይደለም፡፡ ችግሩ የሰው ልጅ ስግብግብ ልቦና፣ ልክስክስ አይን ሲኖረውና አላህን ከማፈር፣ ከሐያእ ሲራቆት ነው። በዚህን ጊዜ አይኑን የመቃብሩ አፈር እንጂ አይሞላውም። ልክ ነብዩ ﷺ ‘የአደምን ልጅ አፈር እንጂ አይኑን አይሞላውም…’ እንዳሉት። ሰውየ! ችግርህ አይንህን አላህ ከከለከለው ነገር አለመስበርህ ነው። ይልቅ ሚስትህን ልክ እንደ ቀድሞዋ (ከአለም ሴቶች ሁሉ ቆንጆ) የምታደርግበትን ዘዴ እንድነግርህ ትፈልጋለህ?” አሉት።
* “አዎ” አለ ሰውየው።
- “አይንህን ስበር!” አሉት ሸይኹ።
ከአንድ ዐረብኛ ፅሑፍ የተመለሰ ነው፡፡
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY AbulAbasNasir (አቡል ዓባስ)

Share with your friend now:
tgoop.com/Abulabas/2247