tgoop.com/Abulabas/2256
Last Update:
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ደስ የሚል ዜና ነው። ጅምላ ፍ-ጅ -ት እያስተናገዱ ላሉት ፈለስጢናውያን ቢያንስ ለተረፉት እፎይታ ነው፣ ምናልባት ዘላቂ የመሆን እድል ካለው። ግን ገዝዛህ አሸነፈች፣ ድል አደረገች እያሉ መደለቅ ሰላቅ አይሆንም ወይ? የድል ትርጉሙ ምን ነበር? እያሸነፈች ከሆነ ተኩስ አቁም ስምምነት ለምን አስፈለገ? እንደ ጀመሩ መጨረስ አይሻልም ነበር?
ከባለፈው አመት ኦክቶበር 7 ጀምሮ 85 ከመቶ ገዝዛህ ፈርሳለች። ከ70 ሺ በላይ ህዝብ አልቋል። ከ120ሺ በላይ ቆስሏል። እየተዋጋ ያለው ቡድን አመራሩን አጥቷል። ኢራንም የድርሻዋን አንስታለች። ሒዝበላት ከዋና ፀሐፊው ጀምሮ በርካታ አመራሩን አጥቷል። ይህ ሁሉ ሆኖም "አሸነፍን" እየተባለ ነው።
ብቸኛው የዚህ ጦርነት አዋንታዊ ጎን በሒዝበላት እና በኢራን መዳከም ሰበብ በሻረል አሰድ ከሰሪያውያን ጫንቃ መውረዱ ነው። ከዚያ ውጭ አይኔን ግንባር ያርገው ካልሆነ በስተቀር ድል የሚባል ነገር ሽታውም የለም። የተለመደ አስቀያሚ ድራማ ነው! ጠላትን ይነካካሉ። በአፀፋው ብዙ ሺህ ህዝብ ያልቃል። ከስንት ተማፅኖና ጥረት በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ይደረጋል። ከዚያ "ገዝዛህ አሸነፈች!" ይባላል። ስንት ዙር ተመሳሳይ ድራማ አለፈ?!
* "ሐ ^ማs ዝም ቢልስ እሷ መቼ ትተዋቸዋለች?" ስትሉ የነበራችሁ ወገኖች! እና የተኩስ አቁሙን ስምምነት ለምን እንደ ድል ትቆጥሩታላችሁ?! አሁን አምናችኋት ነው?
* የሱና ዑለማኦች የረባ አቅም በሌለበት ሁኔታ ጦርነት ውስጥ መግባትን ሲነቅፉ የስድብ ውርጅብኝ ስታወርዱ የነበራችሁ ወገኖች! ለምንድነው ታዲያ የተኩስ አቁሙን ስምምነት እንደ ድል የምትቆጥሩት?! ይሄ እንደሚደርስ ለማንም የሚጠበቅ ነው። ከናንተ በስተቀር ማለቴ ነው።
* jሃ ^ድ ውስጥ ለመግባት ከሰሞንኛ ጀብድ ባለፈ ጠ - ^ላትን መመከት የሚያስችል ዝግጅት ያስፈልጋል ሲባል መረጃዎችን በስሜት እየተነተናችሁ ስታጣጥሉ የነበራችሁ! በተኩስ አቁም ስምምነቱ ስትደሰቱ ምን እያላችሁ እንደሆነ አይገባችሁም?
ለማንኛውም ለጊዜውም ቢሆን እንኳን ሰላም ወረደ። አላህ ዘላቂ ያድርገው። በምርቃና የሚጓዘውን ሁሉ አላህ ልብ ይስጠው። መ^ዥ - ገሩን አላህ ይንቀለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Abul Abas Nasir (አቡል ዓባስ)
Share with your friend now:
tgoop.com/Abulabas/2256