tgoop.com/Alfaruq_islamic/1307
Last Update:
ስለ ጠይረን አባቢል ምን አሳወቀህ?!
@degmolela
እርሱ እንደሌሎች ወፎች እንደሌሎች አዕዋፋት በምድር ላይ ጎጆውን ቀልሶ አይኖርም። ከድንቢጥ ወፍ ከፍ ከእርግብም አነስ ይላል። መልከ ጥቁር ነው። የገዘፉ ዓይኖቹ ጎላ ብለው ሰፊ አፉ ውበትን አላብሰውታል። እግሮቹ ላይ ያረፉት ትላልቅ ጥፍሮቹ ከትንሽነቱ ጋር አይመጣጠኑም። ግዙፍ ናቸው።
የተቀደሰውን ምድር የአላህን ቤት ካዕባን ለማውደም ወደ መካ ያቀናውን የአብርሃ አል አሽረምን ሠራዊት ለማጥፋት ለታላቅ ተልእኮ ታጭተው የተሰጣቸውን ግዳጅ ሊወጡ የመካን ሰማይ እየሰነጣጠቁ ህዋውን አጥለቀለቁ። በቡድን ቡድን ከየአቅጣጫው እየጎረፉ ወደ ውስጥ ዘለቁ። አባቢል ተብለውም ተሰየሙ።
እያንዳንዳቸው በጀሃነም እሳት ውስጥ የተነከሩ ሦስት የሸክላ ድንጋዮችን ይዘው ዘመቱ። ሁለቱን በእግራቸው አንዱን በአፋቸው ታጥቀው በአብርሃ ሠራዊት አናት ላይ ለቀቁት። በአናታቸው ገብቶ በፊንጢጣቸው በኩል እየወጣ የውስጥ አካላቸውን አንድዶ አንፈራፍሮ ይገላቸው ያዘ። የሸሸም ወደ ኋላ ያፈገፈገም አልተረፈም።
ይህ ወፍ ከተልዕኮው በኋላ በቅፅበት እንደታየው ጠፋ። አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር እርሱን ማየት ብርቅ ሆነ። ካልያዙት መሬት አያርፉም። ካላደኑትም በቀላሉ አያገኙትም። የዚህን ወፍ እንግዳዊ አወቃቀር ለማጥናት የአሜሪካ ሳይንሳዊ ተመራማሪዎች እስካሁንም ያድኑታል።
የዘመኑ አብረሀም የአላህን ቤት እያወደመ ነውና ጠባቂው ጌታ ምላሹ የከፋ ነው ኢንሻ አላህ።
BY አል-ፋሩቅ islamic
Share with your friend now:
tgoop.com/Alfaruq_islamic/1307