tgoop.com/Alfaruq_islamic/1312
Last Update:
አንዳንድ ጊዜ ራሴን ከሌሎች ሰዎች ጋር ሳወዳድር ማንም እንደእኔ እድለኛ እና ሙሉ ሰው ያለ አይመስለኝም።
በርግጥም የለም ፣ኢስላም ሙሉ ያደርግሃል ፣ የነብዩ ኡመት መሆን ደግሞ ከሙሉነትም በላይ እድለኝነት ነው።
ነብዩ ለተከተላቸው ሰው ራሳቸውን የቻሉ አንድ ህይወት ናቸው።
ነብዩ ላነበባቸው ሰው ራሳቸውን ችለው በዚህ አለም ላይ አሉ የሚባሉ መፅሀፍት በሙሉ በነብዩ ህይወትና አስተምህሮ ላይ አለ።
አንድ ሰው ታሪክ፣ወይም ልብወለድ አሊያም አነቃቂና ለህይወት መመሪያ ሊሆን የሚችል አንድ መፅሐፍ ብቻ ነው ሊፅፍ የሚችለው።
የነብያችን ግን ከዚህ ይለያል ፣
ለምሳሌ መገሰፅ፣ማነቃቃት፣ሁሉም ነገር ያካትታል። ነብዩ ሲያስተምሩ ያልዳሰሱት ነጥቦ ያላነሱት ርዕስ የለም።
ከነዛ ውስጥ የህይወት መመሪያ የሚሆን አስተምህሮት እንኩላችሁ ልላችሁ ወደድኩ።
♦️የመኝታ ሰርዓቶች
➖➖➖➖➖➖➖
➡️ከመተኛት በፊት በር እቃዎችን መዘጋጋት መከዳደንና እሳት ማጥፋት፣-
ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል እቃዎችን ከዳድኑ ፣ኮዳዎችንም እሰሩ ፣በሮችንም ዝጉ ሰይጣን የታሰረን አይፈታም። የተዘጋን በር አይከፍትም፣ የተከደነንም አይከፍትም።መክደኛ ካጣችሁ እቃችሁ ላይ እንጨት አድርጋችሁ ቢሆን እንኳን የአላህን ስም ጥሩበት ።እሳትንም አጥፉ አይጥ ቤታችሁ ታቃጥላለች ።
➡️ጀናባ ከሆነ ውዱዕ አድርጎ መተኛት፣-
አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እንድህ ብላለች ነብዩ ስለሏ አለይሂ ወሰለም ጀናባ ሆነው መተኛት ሲፈልጉ ውዱዕ ያደርጉ ነበር።
➡️ፍራሹን ጠረግ ማድረህ፣-
ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ለመተኛት ወደ ፍራሻችሁ ስትቀርቡ በሽርጣችሁ ውስጠኛውን ክፍል ሶስት ግዜ ጠረግ አድርጉት።
➡️ቤት ውስጥ ለብቻ አለመተኛት፣-
አብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም ለብቻ መተኛትና ለብቻ ጉዞ መውጣት ከልክለዋል።
➡️ውዱዕ ማድረግ
ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ወደ መኝታ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርግ።
➡️የመኝታ አዝካሮችንና የተወሰኑ የቁርአን አንቀጾች ማንበብ፣-
♦️ከቁርአን
ፋቲሃ ፣አየተል ኩርሲይ ፣ የበቀራ የመጨረሻ ሁለት አንቀጾች ፣ ሱረት ካፊሩን ፣ሱረት ኢኸላስ ፣ሱረት ፈለቅ፣ ሱረት ናስ፣ ከተቻለ ሌሎችም የአላህ መልእክተኛ ሲተኙ ያነቧቸው እንደነበረ የተዘገቡ አንቀጾችን ማንበብ።
አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ እንዳስተላለፈችው፣የአላህ መልእክተኛ ዘወትር ሌሊት ሲተኙ ፣
👈قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلْفَلَقِ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ
እነዚህን በማንበብ እጃቸው ላይ ሶስት ሶስት ግዜ ተፍተው ከራሳቸውና ከፊታቸው በመጀመር የደረሱትን ያህል አካላቸውን ያብሱ ነበር።
♦️ከአዝካሮች
👈 بِاسْمِكَ رَبِّ وَضَعْتُ جَنْبِي وَبِكَ أَرْفَعُهُ، إِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِي فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِين
▪️ትርጉም ፣- ጌታየ በስምህ ወገቤን አሳረፍኩ በስምህም አነሳዋለው፣ነፍሴን ከያዝካት እዘንላት ፣ከለቀካትም መልካም ባሮችን በምትጠብቅበት ጠብቃት።ሌሎችንም አዝካሮች ማለት--
➡️በቀኝ ጎን መተኛት
ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል፣- ወደ መኝታህ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርገህ በቀኝ ጎንህ ተኛ።
➡️በሆድ አለመተኛት
ነብዩ ስለሏ ሁአለይሂ ወሰለም በሆዱ ተኝቶ ላዩት ሶሃባ ተነስ ይህ አተኛኝ አላህ የማይወደው ነው ብለውታል።
♦️መተኛትህ ካልቀረ በሱና ላይ ሁነህ ተኛ
👉ሱና የዱንያም የአሔራ ብርሀን ነው።
✅ህይወት ያለ ሱና ድቅድቅ ጨለማ ነው።
ሼር አድርጉት
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
BY አል-ፋሩቅ islamic
Share with your friend now:
tgoop.com/Alfaruq_islamic/1312