tgoop.com/Alfaruq_islamic/1333
Last Update:
ዩሱፍ ዐሰ በሚኖርበት የቤተመንግስት ህንፃ ላይ ሁኖ ወደ ከተማው ጎዳና ቁልቁል ሲመለከት አንድ የተጎሳቆለ እና ልብሱ የተቀዳደደ ወጣት ከእይታው ገባ።
ዩሱፍ ዐሰ ልቡ አዘነ። ከቆመበት ወጣቱን በመመልከት ላይ ሳለ ጂብሪል ዐሰ ብቅ አለ ና፦‹‹የአላህ ነቢይ ሆይ! ይህን ወጣት ታስታውሰዋለህን?›› ሲል ጠየቀው።
‹‹አላስታውሰውም?›› ሲል መለሰለት።
ጂብሪልም ዐሰ ቀበል አድርጎ፦‹‹ያኔ ትዝ ይልሃል! የንጉሱ ሚስት በቅጥፈት ልታስፈርድብህ ብላ በወነጀለችህ ግዜ ከቅጣት የታደገህ ህፃኑ መስካሪ?›› ሲል ጠየቀ።
‹‹አዎን ያን ክስተት አልረሳውም›› ሲል ዩሱፍ ዐሰ መለሰ።
‹‹ታድያ ይህ ወጣት እኮ ያኔ የመሰከረልህ ልጅ ነው›› ብሎ ጂብሪል ዐሰ ነገረው።
ዩሱፍ ዐሰ ይህንን ልጅ በዚህ ሁኔታ በመመልከቱ እጅግ አዝኖ ጠባቂዎቹን ይዘውት እንዲመጡ ልኳቸው ወጣቱን በትልቅ ዝግጅት ተቀብሎ እና አልብሶ ይንከባከበው ጀመር።
ይህን ድርጊት ይመለከት የነበረው ጂብሪልም ዐሰ የአግራሞት ሳቅ እየሳቀ ትዕይንቱን ቀጥሏል።
ዩሱፍም ዐሰ የጂብሪልን ሳቅ አይቶ፦‹‹ወጣቱን በሚገባ ክብር ስላልተንከባከብኩት ነው ምትስቀው?›› ሲል ጠየቀ።
ጂብሪልም ዐሰ እንዲህ አለ፦‹‹አንተ በህይወት ዘመንህ አንዲትን ምስክር ለሰጠህ ግለሰብ ይህን ያህል ከተንከባከብክ፤ አላህን በየእለቱ ለሱ ጌትነት የሚመሰክሩ ባሮቹን እንዴት ያከብር ይሆን ብዬ ነው››
@Alfaruq_islamic
BY አል-ፋሩቅ islamic
Share with your friend now:
tgoop.com/Alfaruq_islamic/1333