tgoop.com/Alfaruq_islamic/1336
Last Update:
ሸይኹ’ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ-ያህ እንዲህ ይላሉ፦
«ክህደት፣ አመፅና ትዕዛዝን መጣስ የክፋትና የጠላትነት መነሻ (መሆኑ የታወቀ) ከሆነ፦ ምናልባት አንድ ግለሰብ ወይም ጭፍራ ጥፋት ያጠፋና ሌሎች (ጥፋተኞቹን በመልካም) ከማዘዝ ወይም (ከመጥፎ) ከመከልከል በዝምታ ይታቀባሉ፤ ይህም ከወንጀላቸው ይመደባል! ሌሎች ደግሞ በተከለከለ መልኩ ያወግዟቸዋል፤ ይህም ከወንጀላቸው ይመደባል! ከዚያም መከፋፈል፣ መለያየትና ችግር ይከሰታል! ይህ ድሮም ሆነ ዘንድሮ ከታላላቅ ፈተናዎችና ችግሮች አንዱ ነው!...»
[“አሊ’ስቲቃማህ” በተባለው መፅሃፋቸው ገፅ 481 ላይ እንዳሰፈሩት (የ“ዳሩ’ል-ፈዲላህ” ህትመትን መሰረት ያደረገ)]
ﻗﺎﻝ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ :
ﻭﺇﺫﺍ ﻛﺎﻥ ﺍﻟﻜﻔﺮُ ﻭﺍﻟﻔﺴﻮﻕ ﻭﺍﻟﻌﺼﻴﺎﻥ ﺳﺒﺐَ ﺍﻟﺸﺮّ ﻭﺍﻟﻌﺪﻭﺍﻥ ﻓﻘﺪ ﻳُﺬﻧﺐ ﺍﻟﺮﺟﻞ ﺃﻭ ﺍﻟﻄﺎﺋﻔﺔ ﻭﻳﺴﻜﺖ ﺁﺧﺮﻭﻥ ﻋﻦ ﺍﻷﻣﺮ ﻭﺍﻟﻨﻬﻲ؛ ﻓﻴﻜﻮﻥ ﺫﻟﻚ ﻣﻦ ﺫﻧﻮﺑﻬﻢ، ﻭﻳﻨﻜﺮ ﻋﻠﻴﻬﻢ ﺁﺧﺮﻭﻥ ﺇﻧﻜﺎﺭًﺍ ﻣﻨﻬﻴّﺎ ﻋﻨﻪ؛ ﻓﻴﻜﻮﻥ ﺫﻟﻚ ﻣﻦ ﺫﻧﻮﺑﻬﻢ؛ ﻓﻴﺤﺼﻞ ﺍﻟﺘَّﻔَﺮُّﻕُ ﻭﺍﻟِﺎﺧْﺘِﻠَﺎﻑ ﻭﺍﻟﺸَّﺮ، ﻭﻫَﺬﺍ ﻣﻦ ﺃﻋﻈﻢ ﺍﻟْﻔِﺘَﻦ ﻭﺍﻟﺸﺮﻭﺭ ﻗَﺪِﻳﻤًﺎ ﻭﺣﺪﻳﺜًﺎ
ﺍﻻﺳﺘﻘﺎﻣﺔ ( ﺹ 481- ) ﻁ - ﺩﺍﺭ ﺍﻟﻔﻀﻴﻠﺔ
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic
BY አል-ፋሩቅ islamic
Share with your friend now:
tgoop.com/Alfaruq_islamic/1336