Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/Alfaruq_islamic/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
አል-ፋሩቅ islamic@Alfaruq_islamic P.1338
ALFARUQ_ISLAMIC Telegram 1338
ተቀድመካል!

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ቀን ሰሐቦቻቸውን መስጂድ ውስጥ ሰብስበው ንግግር እያደረጉላቸው ነው። በዚህ መሐል :- "ከህዝቦቼ መካከል ሰባ ሺህ የሚሆኑት ያለ ምርመራና ያለ ቅጣት ጀነት ይገባሉ።" አሉ። አጋጣሚውን መጠቀም የነበረበት ዑካሻህ ኢብኑል ሚሕሰን ቀልጠፍ ብሎ :- "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህ ከእነርሱ መካከል እንዲያደርገኝ ለምኑልኝ!" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም :- "አንተ ከእነርሱ ነህ!" አሉት። ከስብስቡ መካከል አንድ ሰውዬ ተነሳና :- "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እኔንም ከእነርሱ መካከል እንዲያደርገኝ ለምኑልኝ!" ሲላቸው "በርግጥ በዑካሻህ ተቀድመሃል" በማለት መለሱለት።

አምላካችን አላህ የሰሐቦችን ደረጃ ሲገልጽ የመጀመሪያውን ደረጃ ተርታ ቀዳሚ ያደረገው ኢሥላምን በመቀበል ቀዳሚ የነበሩትን ነው።

وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ
(ሱረቱ አል-ተውባህ - 100)
ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች

ዕድልህን ተጠቀምበት። መልካም ነገር ስታገኝ "በኋላ እሰራዋለሁ!" እያልክ አትዘናጋ። ሙዕሚን ምን ጊዜም መልካም ነገር ሲገጥመው ፈጥኖ ዕድሉን የተጠቀመበት ቢሆን እንጂ አያሳልፈውም። የትኛው ስራህ ለጀነትህ ቁልፍ እንደሆሚሆን አታውቀውም።

فَاسْتَبِقُوا الْخَيْرَاتِ

[ አል-በቀራህ - 148 ]
ወደ መልካም ሥራዎችም ተሽቀዳደሙ፡፡

በተለይ ጉዳዩ አኺራዊ ከሆነ አይንህን እንኳ በማሸት ጊዜህን አታባክነው። ጀነትን በመግባት የሚቀድመው በኸይር ስራ የሚሽቀዳደመው ነው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል :-
وَالسَّابِقُونَ السَّابِقُونَ

[ ሱረቱ አል-ዋቂዓህ - 10 ]
(ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡

ሁሌም ንቁና ጠንካራ ማንነት ይኑርህ። ኸይር ስራዎች ላይ መቻኮል የነብያት መገለጫ እንደሆነ አታውቅም እንዴ?

إِنَّهُمْ كَانُوا يُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَيَدْعُونَنَا رَغَبًا وَرَهَبًا ۖ وَكَانُوا لَنَا خَاشِعِينَ

(ሱረቱ አል-አንቢያ - 90)
እነርሱ (ነቢያት) በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ኾነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡
-----------------------------------------------

✍️ወንድም አቡ ሩመይሳ

https://www.tgoop.com/Alfaruq_islamic

tgoop.com/Alfaruq_islamic/1338
Create:
Last Update:

BY አል-ፋሩቅ islamic

Share with your friend now:
tgoop.com/Alfaruq_islamic/1338

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Write your hashtags in the language of your target audience. The group’s featured image is of a Pepe frog yelling, often referred to as the “REEEEEEE” meme. Pepe the Frog was created back in 2005 by Matt Furie and has since become an internet symbol for meme culture and “degen” culture. Matt Hussey, editorial director of NEAR Protocol (and former editor-in-chief of Decrypt) responded to the news of the Telegram group with “#meIRL.” Select “New Channel” You can invite up to 200 people from your contacts to join your channel as the next step. Select the users you want to add and click “Invite.” You can skip this step altogether.
from us

Telegram አል-ፋሩቅ islamic
FROM American