tgoop.com/Alfaruq_islamic/1412
Last Update:
⌛እንግዲህ ሻዕባን ገብቷል በሌላ ቋንቋ ታላቁ ረመዳን እንደገባ ብንቆጥረው የተሻለ ነው። ረመዳን እየመጣልን ነው ብሎ መቁጠር ሳይኾን እኛ ወደ ረመዳን እየሄድን ነው ብሎ ማሰብ ይጠቅመናል። በዚሁ ማንነት ደጃፉ ላይ ቀርበናል። ቀድሞ ረመዳን ውስጥ የገባ ዕድለኛም አለ። ረመዳን ከገባ በኋላም ዘግይቶ ወደ ረመዳን የሚደርስ አለ። ረመዳንን ሳያገኘውም ሳይጠቀምበት የሚወጣው አለ! ረመዳንን አግኝቶ ሳይጠቀምበት የወጣ ሰው ላይ ጂብሪል እርግማን አውርዷል ረሱልም አሚን ብለዋል።
⌛ቁርአን የሚለው "ወደ አላህ ሽሹ ነው!" ነፍሲያችን ደግሞ ተግባሯ ሲታይ "ከአላህ ሽሹ የሚል ነው! የሚመስልባት😐 ግድ የለም ውስን ቀናት አሉን፤ ብንን ብለው ከማለቃቸው በፊት አቅጣጫችንን እናስተካክል። ነፍስን ከሚያቆሽሽ ቂለ ወቃል እንውጣና ነፍስን ወደ ማከም እንመለስ።
ለረመዳን የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ከማዘጋጀት በላይ መንፈሱን ለማግኘት ራሳችንን እናሰናዳ! በተቀሩት ቀናት ቁርዓን እና የለሊት ስግደት ላይ በሚገባ እንሰነቅ ፣ ከአላህ ምሕረት ለማግኘት የሚያነሳሳን ቦታ ላይ እንገኝ።
⌛ኢብኑል ቀይም በዚህ ጉዳይ ሲመክሩን እንዲህ ይሉናል ፦ « ቁርዓንን ማስተንተን እና በመጨረሻው ለሊት አላህን አብዝቶ መማጸን ለልብ ሕያው መሆን ቁልፍ ነገሮች ናቸው። »
⌛በረመዳን ደጃፍ ላይ ሆነን ዝንጉ የሆንን ከመሰለን መድሐኒቱ ዚክር ነው። ከዚክሮች ሁሉ ቁንጮው ቁርዓን ነው ። ረመዳን ዛሬ እንደገባ እናስብ፣ ሁለመናችንን እንዲያስተካክልልን አላህን እንለምነው። አላህ ይህን ችሮታውን ይለግሰን ፤ ድክመታችንን በጥንካሬ ይለውጥልን
⌛በረመዳን የሚጠቀመው ረመዳን ከመምጣቱ በፊት ወደ ረመዳን የሄደ ብቻ ነው!
BY አል-ፋሩቅ islamic
Share with your friend now:
tgoop.com/Alfaruq_islamic/1412