tgoop.com/Alfaruq_islamic/1419
Create:
Last Update:
Last Update:
በሰላት መሰላቸት
አንድ ሰው ሸሀዳ ሲይዝ ጀነት ውስጥ በጣም ሰፊ #ቦታ (ግዛት) ይመራል ይህ ቦታ በርካታ ነገሮች ሊኖረው ይገባል ይህ የሚሟላው በመልካም ስራ ልክ ነው ስለዚህ በርካታ መልካም ስራ ልንልክ ይጠበቃል አለበለዛ ምድረበዳ ይሆናል
ለዱንያ ስራ በየቀኑ ለብዙ ሰአት #እንለፋለን በቀን ቢያንስ ሶስት ጊዜ እንበላለን አይሰለቸንም ግን በሰላት እሰለቻለን, የምናገኘውን ምንዳ ብናቅ ኖሮ እንኳን ፈርዱ ሱናው አይቀረንም ነበር ስለዚህ ምንዳውን እያሰብን እንበርታ
#ሰላት በትርፍ ጊዜ ወይም አንዳንድ ጊዜ የሚፈፀም ሳይሆን በወቅቱ በመደበኛነት መደረግ ያለበት ኢባዳ ነው ምክንያቱም የቀልብ ምግብ ናት ኢማናችን እንዳይሞት ትከላከላለች.
ነብዩ (ሰአወ )
إِنَّ أَوَّلَ مَا يُحَاسَبُ بِهِ الْعَبْدُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ مِنْ عَمَلِهِ صَلاَتُهُ فَإِنْ صَلُحَتْ فَقَدْ أَفْلَحَ وَأَنْجَحَ وَإِنْ فَسَدَتْ فَقَدْ خَابَ وَخَسِرَ
አንድ አማኝ የፍርዱ ቀን መጀመሪያ የሚተሳሰበው ሰላቱን ነው. ሰላቱ ከተሟለች ውጤታማ ይሆናል (ነጃ ይወጣል) ከተበላሸች ግን ይከስራል. ቲርሚዚይ
BY አል-ፋሩቅ islamic
Share with your friend now:
tgoop.com/Alfaruq_islamic/1419