ALWANE_COLORS Telegram 2267
🎡 ጣፍጭ የሆኑ የሳሀቦች ታሪክ 🎡

🍂 ክፍል 6

(ሑዘይፋ ረዲየላሁ አንሁ)

*የሑዘይፋ ረ.ዐ የስለላ ተልዕኮ

~ ሑዘይፋ ረ.ዐ እንደገለፀው :- ''በኸንደቅ ጦርነት ግዙፍ የጠላት ጦር ጋር መጋፈጥ ነበረብን። የመካና የአጎራባች ጎሳዎች ስብስብ ኃይል ወሮናል። የመዲና አይሁዳውያን በኒ ቁረይዟ ከጀርባችን ሊወጉን በዝግጅት ላይ ነበሩ። ሁላችንም መዲናን ከጥቃት ለመከላከል በመውጣታችን ቤታችንን እና ቤተሰባችንን እንደሚዘርፉና እንደሚያስቸግሩ ተሰምቶናል። መናፍቃን ወደ መዲና ለመመለስ ነብዩን ﷺ ፈቃድ መጠየቅ ጀመሩ። ቤቶቻቸው ያለ ጠባቂ የቀሩ መሆናቸውን ና በአይሁዳውያንም ሊጠቁ ስለሚችሉ ጥበቃ እናድርግ የሚል የሀሰት ምክንያት አቀረቡ።

~ ለሁሉም ፈቃድ ሰጡ። በእነኛ የፈተና ቀናት አንድ ምሽት ከሌላው ጊዜ የተለየ የጨለማና ንፋስ ነበር። ከጨለማው ከፍተኝነት የተነሳ አንድ ሰው የገዛ እጁን እንኳን ማየት አይችልም ነበር። ንፋሱም እጅግ አደገኛ ነበር። መናፍቃን ወደ መዲና በመመለስ ላይ ናቸው። ሦስት መቶ ሰዎች ብቻ በተጠንቀቅ ለመወጋት ተዘጋጅተናል። ነብዩ ﷺ ወደ እያንዳንዳችን በመጠጋት ይጠይቁናል ። እኔ ራሴን የምከላከልበት የጦር መሣሪያ አልነበረኝም። ከብርድ የሚያድነኝ ልብስም አልነበረኝም። አንድ ትንሽ ፎጣ ቢጤ ብቻ ነበረኝ ከሚስቴ የተዋስኩት። ከጉልበቴ ሎሚ ላይ ጠመጠምኩት። ከዚያም በጉልበቴ ተንበረከኩ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በአጠገቤ ሲያልፉ ' ማንነህ?' አሉኝ:- 'ሑዘይፋ ነኝ ' አልኳቸው።

~ ከብርዱ የተነሳ መቆም አልቻልኩም። ሀፍረት እየተሰማኝ ጉልበቴን ከመሬቱ ጋር ቸክዬ ቀረሁ። እርሳቸው ግን :- ''ሑዘይፋ ተነስ! ወደ ጠላት ካምፕ በመሄድም መረጃ ሰብስበህ ተመለስ ' አሉኝ። ከሁሉም ሶሓባ ለጠላት መመከቻ መሣሪያ የሌለኝ ፤ ራሴን ከብርድ ለመከላከልም ልብስ የሌለኝ እኔ ነበርኩ። ቢሆንም በፍጥነት በመነሳት ወደ ጠላት ካምፕ አመራሁ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት ጸለዩልኝ:- '' አላህ ሆይ! ከሁሉም አቅጣጫ አንተ ጠብቀው።' በቅጽበትም ፍርሃቴና ቅዝቃዜው ልቀቀኝ ።በሞቃታማ ና ሰላማዊ ክልል የምጓዝ መሰለኝ። ነብዩም ﷺ 'እነርሱም የሚሠሩትን ካጤንክ በኋላ በቶሎ ተመለስ። ሌላ እርምጃ እንዳትወስድ።' አሉኝ።

~ በጠላት ካምፕ ስደርስ የሚቀጣጠል እሳት ተመለከትኩ። ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠዋል። እያንዳንዱ ሰው እጁን በእሳቱ እያሞቀ ሆዱን ያሻል። የማፈግፈግ ድምጽ በሁሉም አቅጣጫ ይሰማል። ሁሉም ለጎሣ አባላት ዕቃቸውን እንዲጭኑና እንዲሸሹ በማሳሰብ ላይ ነው።

~ ድንኳናቸው በነፋስ ኃይል በሚገፉ ድንኳኞች ተነረተ። የድንኳኖቹ ገመድም ተበጣጠሱ። እንስሳዎች ቅዝቃዜውን መቋቋም ተስኗቸው መሞት ጀመሩ ። የጠላት ጦር አዛዥን አቡ ሱፍያንን ተመለከትኩት። ከእሳት አጠገብ እጁን በማሞቅ ላይ ነበር። ልገድለው አሰብኩ። ቀስቴን አነጣጠርኩ ። በቅጽበት ግን የነብዩን ﷺ ትዕዛዝ አስታወስኩ ። ቀስቴን ወደ ቦታው መለስኩ። በመካከላቸው ባለሁበት ወቅት ባዕድ ኃይል ሊኖር እንደሚችል የጠረጠሩ ይመስለኛል ። አቡሱፍያን ' በመካከላቸው ሰላይ እንዳይገባ። እያንዳንዳችሁ ከአጠገባችሁ ያለውን ሰው እጅ ያዙ።' በማለት ለፈለፈ ። በአጠገቤ ያለውን ሰው እጅ በቅፅበት በመጨበጥ ' አንተ ማን ነህ!' አልኩት።' እንዴ አታውቀኝም እገሌ እኮ ነኝ' አለኝ።

~ ከዚያም ወደ ነብዩ ﷺ ተመለስኩ ። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሶላት ላይ ነበሩ። ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ምን ጊዜም የሚያቀኑት ወደ ሶላት ነው። ሶላት ሰግደው እንደጨረሱ በጠላት ካምፕ ያየሁትን በዝርዝር አቀረብኩላቸው ።

~ ሰላይ በመካከላችሁ ገብቷል በማለት ሰላዩን ለመያዝ ያደረጉትን ጥረት እንዴት እንዳከሸፍኩ ስነግራቸው የሚያምር ጥርሳቸውን መመልከት ችያለሁ...''። ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ ያረሱለላህ !!

እኛም በጀነት ፊታቸውን ከነ ፈገግታቸው ከሚያዩት ያድርገን አሚን🤲

#Bint_nassir

@Alwane_colors
@Alwane_colors
@Alwane_colors

tgoop.com/Alwane_colors/2267
Create:
Last Update:

BY 🌴Ãlwan .... ️ الون ️

Share with your friend now:
tgoop.com/Alwane_colors/2267

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Today, we will address Telegram channels and how to use them for maximum benefit. Other crimes that the SUCK Channel incited under Ng’s watch included using corrosive chemicals to make explosives and causing grievous bodily harm with intent. The court also found Ng responsible for calling on people to assist protesters who clashed violently with police at several universities in November 2019. Ng was convicted in April for conspiracy to incite a riot, public nuisance, arson, criminal damage, manufacturing of explosives, administering poison and wounding with intent to do grievous bodily harm between October 2019 and June 2020. Just at this time, Bitcoin and the broader crypto market have dropped to new 2022 lows. The Bitcoin price has tanked 10 percent dropping to $20,000. On the other hand, the altcoin space is witnessing even more brutal correction. Bitcoin has dropped nearly 60 percent year-to-date and more than 70 percent since its all-time high in November 2021. Done! Now you’re the proud owner of a Telegram channel. The next step is to set up and customize your channel.
from us

Telegram 🌴Ãlwan .... ️ الون ️
FROM American