tgoop.com/ArkemMy/456
Last Update:
📿𝐑𝐚𝐦𝐚𝐝𝐚𝐧......😊8
ረመዳን 8🌙
የሰደቃ ወር
ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ
«አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ (ለሰዎች) መልካምን አድርግ፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና»
ሰደቃ ደረትን ያሰፋል…… ለቀልብ እረፍት ይሠጣል
(ረሱል ሰዐወ) ስለ ስስታምና ለጋሽ ሰው ምሳሌ ሲያስቀምጡ፡-
ምሳሌያቸው ከብረት የሆነ ጡሩር ደረታቸው ላይ እስከ አንገታቸው ድረስ
እንደለበሱ ሁለት ሰዎች ነው፡፡ ለጋሹ ሰውዬ በለገሰ ቁጥር ትሰፋለታለች፡፡
ቆዳውም እስኪሸፈን ድረስ ታለብሰዋለች፡፡
ስስታም ሰው ደግሞ አንድን ነገር ለመስጠት ባሰበ ቁጥር እሱ ማስፋት ቢፈልግም እንኳ እያንዳንዷ ቀለበት ቦታዋን ጥብቅ እንቅ አድርጋ ትይዛለች፣ አትሰፋም፡፡› ብለዋል፡፡
ሰደቃ የአላህን ሱብሃነሁ ወተዓላ ቁጣ ታበርዳለች፡፡ የአላህ መልእክተኛ
ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “በሚስጢር የምትሰጥ ሰደቃ የልዕልና ባለቤት የሆነውን የአላህን ቁጣ ታበርዳለች፡፡” ብለዋል፡፡
“ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሁሉ ሶደቃም ወንጀልን /ሐጢኣትን/
ታጠፋለች፡፡”
“በየቀኑ ባሮች በሚያነጉበት ቀን ሁለት መላእክት ይወርዳሉ፡፡ አንደኛው ‹አላህ
ሆይ ለሚለግስ ሰው ተካለት፡፡› ይላል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ‹አላህ ሆይ! የሚሰስትን ሰው አጥፋበት፡፡› ይላል፡፡”
ሰደቃ የሚሰጥ ሰው ሀብትና ገንዘቡ ይባረክለታል፡፡
የአላህ መልእክተኛ ሰዐወ “ሰደቃ ከሀብት አንዳችም ነገር አይቀንስም፡፡” ብለዋል ፡፡
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
@ArkemMy
BY Arqem[አርቀም]
Share with your friend now:
tgoop.com/ArkemMy/456