tgoop.com/ArkemMy/470
Last Update:
**የደቂቃ ማስተዋልን ወስደህ ተመለስ**
የደቂቃ ፍፁም ፀፀትህ፤ የቅፅበት እውነተኛ መመለስህ ላንተ እኮ በቂህ ነበር፤ የጌታህ ምህረት እጅጉን ቅርብ ነውና። አንተ ግን ተዘናጋህ!!
ለዘመናት በዝንጋቴዎችህ ውስጥ ሸይጣን የማይፈርስ የሚመስል ቤቱን እለት በእለት በወታደሮቹ እየገነባ ከጌታህ በጠንካራ መሰል ግንብ ሊያርቅህ ይለፋል። እያንዳንዱ ዝንጋቴህ፣ ስህተትህና ውድቀትህ በዙሪያህ ለሚገነባው አጥር ጡቦች ናቸው።
ይህ የዘመናት ግንብ ግን የጌታህን ምህረት በከጀሉ እውነተኛ የፀፀት እምባዎች ይወድማል፤ ወደ ኃያሉ አምላክህ መመለስን ፍፁም ቁርጠኛ በሆኑ የደቂቃ ጥሪዎች እንዳልነበር ይሆናል፤ የማይፈርስ የመሰለው ከልካይ ቤትም ፈርሶ ዳግመኛ በጌታህ ፍቅር ታብባለህ። ምንም ቢገዝፍ የሸይጣንና ወታደሮቹ ግንብ ፈራሽ ነውና!
ኢብኑ አል ቀይም አል ጀውዚያህ እንዲህ ሲል ተቀኝቶ ነበር።
بنى ما بنى حتى إذا ظن
إن ما بناه وطيد راسخ الأسس محكم
أتى العفو من كل القواعد ما بنى
فخر عليه سقفه المتهدم
ولو أن ألفا من بناة جنوده
بنوا كل يوم ألف بيت ورمموا
لهدت بيوت الكل توبة مخلص
على ما جناه وصح منه التندم
BY Arqem[አርቀም]
Share with your friend now:
tgoop.com/ArkemMy/470