tgoop.com/Bookshelf13/6260
Last Update:
በኢትዮጵያዊ ሁለ ውስጥ የሞላ፣
______
(ልብ የሚሞላ ቅድስና!)
እኔ ግን የቱንም ያህል ተቃራኒ እውነታ ለትንግርት ቢከመር በዚህች ሀገር ተስፋ አልቆርጥም!
ይቺ ሀገራችን የሆነ የምትኖርበት ምሥጢር አላት። የሆነ ተዓምር አምቃለች። የሆነ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ዝም ብሎ በአየሩ ላይ እየተንሳፈፈ የሚኖር አንዳች ጥልቅ ምሥጢር አለ።
የሆነ በመጨረሻ ከመጨረሻው የከፋ ነገር የሚከልለን ተዓምር አለ። ይሄ ሁሉ ዘመናዊው ዓለም ሄዶ ሄዶ ቢጠፋ፣ ቢጠፋፋ፣ የሆነ እንዲቀርልን የተፈለገ፣ እንድንተርፍበት፣ እንድንጠበቅበት የተፈለገ አንዳች መንፈሳዊነትን የተላበሰ ነገር አለ በኢትዮጵያችን።
ብዙ ጊዜ የማስበው ነገር ነው ይህ። ደሞ የማገኛቸው ድርሳናት ሁሉ ይሄንኑ የሚያጠናክሩልኝ ናቸው። የሆነ ዘመኑን የሚጠብቅ ታላቅ ትንሳዔ አለ በምድራችን።
ትንቢት አይደለም ይህ። ብዙ ጥናቶች፣ ምርምሮች እየደጋገሙ የሚሙጡበት ድምዳሜ ነው። ይመጣሉ፣ ይመረምራሉ፣ መንገዶች ሁሉ ወደኛ ያመራሉ።
ከዚያ ግን ሲመጡ አያገኙትም። ልክ የበረሃ ውሃ በአሸዋ ውስጥ ሠርጎ እንደሚጠፋ፣ የሆነ ቦታ ላይ ሲደርሱ ዳናው ይሰወርባቸዋል። But they can feel it. They know in their hearts that there's something sacred in this land!
There's something continuing from the ancient in the spirits of these people ይሉናል ሲደመድሙ ስለኛ።
የሙሴ ፅላት እኛው ጋር አለ። ቅዱስ ፅዋው እኛው ጋር ነው። ታቦቱ የእሱም አቅጣጫ እኛው ጋር ነው የሚያመላክተው። ግማደ መስቀሉ እሱም አለ በዚህችው ምድራችን ላይ።
የቀደሙት ሁሉ ነገሥታት ባህሩንና ውቅያኖሱን ሁሉ አጥብቀው የሚሸሹ ናቸው። ይህን ነገር ከየትም አላገኘሁትም። ግን ደጋግሜ ራሴን የምጠይቀው ጥያቄ ነው።
ለምንድነው ለሺህ ዓመታት ምስጢራቸውንና ምድራቸውን እየተከላከሉ የቆዩ ቀደምቶቻችን ከጠረፉ እና ከባህሩ ይልቅ ወደ heartlandዱ፣ ወደ መሐል እምብርት ምድራቸው ማፈግፈግን የሚመርጡት? የሆነ የሚያውቁት ምሥጢር መኖር አለበት! እንደዚያ ይመስለኛል ታሪካቸውን ስመለከት።
የሆነ ሊመጣባቸው ያለ መቅሰፍት የታያቸውና የሚያውቁ ነው የሚመስሉት። ደግመው ደጋግመው ወደ ተራሮችና ወደ መሐል እምብርት ውስጥ ወደታነፁ ገዳማት፣ በረሃዎች፣ ሃይቆችና ደሴቶች ሥርቻ ውስጥ መሸሸግን ይመርጣሉ።
የሆነ ወደፊት የሚመጣ የዓለም ጥፋት ያለ እና በዚህች ቅዱስ ምድር ተጠልለው የሚያመልጡ ነው የሚመስለው።
ይህች ምድራችን በመጨረሻው የዓለም ጥፋት የኖህ መርከብ ሆና የሰው ዘር የሚተርፍባት ቅድስት ምድር ትመስለኛለች። There's something mysterious about our whole existence and ways of life!
ለማንኛውም እነዚህ የሙሴን ፅላት አድራሻ ከየዓለሙ ሁሉ ጥግ ሊያፈላልጉ የተነሱ ሁለት በዓለም የታወቁና በኢትዮጵያ ምሥጢራት ጉዳይ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ክብር የተቸራቸው ተመራማሪዎች፣ ብዙ ነገሮችን ያስሱ፣ ይፈነቅሉና... በመጨረሻ የሙሴ ፅላት በየዓለሙ ሁሉ አለ ይባላል። ግን በኛ እምነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፅላት እውነተኛው ፅላት ነው ይላሉ።
ይህን ልንል የቻልነው ደሞ መንፈሱ በሀገሪቱ ሁለመና ሰፍፎ በግልፅ የሚታይ፣ በቀልብህ የሚገባ፣ የሚታወቅህ... ስለሆነ ጭምር ነው ይላሉ።
ወደ አንድ የኢትዮጵያኖች መንፈሳዊ በዓል፣ ወይ ቅዳሴ፣ ወይ አኗኗር፣ ወይ አክሱም፣ ወይ ላሊበላ፣ ወይ የሰዉ ልብስና አኗኗር፣ ወይ ወደ ጎጆ ቤቶቻቸው፣ ወይ ሐይማኖቱ ምንም ይሁን ኢትዮጵያኖችን ልብለህ እያቸው እስቲ? ይላሉ።
በየሰዉ ውስጥ የምታየው በዘመናዊው ምዕራባዊው ዓለም የረከሰ ቁሳዊ ግልሙትና የማይደረመስ አንዳች ዓይነት ከሺህዎች ዓመታት በፊት ብቻ ልታገኘው የምትችለው የተቀደሰ ጥንታዊ ሥሪት አለ በየሰዉ ሁሉ የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ ያረበበ።
እውነት ይመስለኛል። ዓለምን ሁሉ እንመስላለን። ዓለምን ሁሉ እንወክላለን። ተቀይጠናል። ከዓለሙ ጋርም፣ እርስ በርሳችንም። ግን እንለያለን። ዓለም ሲጠፋፋ በመጨረሻ በፅላቱ ተዓምር የምንተርፍ እኛ ሳንሆን አንቀርም!
የእጣናቸው ሽታ ራሱ ወደሆነ ጥንታዊ ዓለም ይወስደኛል ይላል አንደኛው ተመራማሪ🙏🏿! ፈገግ አልኩ። አንተ ዕጣን ትላለህ፣ ጥንታዊውን መንፈስ ያልተሸከመ ምን ነገር አለ በምድራችን?
ጠጅ ሣሩና አሪቲውስ? ቄጠማና ሉባንጃውስ? ያገር ልብሱስ? ሹሩባውስ? ተነፋነፍና ጥልፍ ቀሚሱስ? ምጣድና አክንባሏችንስ? ጊርጊራና ማራገቢያዎቹስ? ምድጃና ከሰሉስ? ኩሽናችንስ? ሁሉነገራችንስ?
ከመላው አፍሪካ ተነጥለን፣ በሌሎች ዓለማት ገዢዎች ዋና ጥንታዊ ሥሪታችን እንዲጠፋብን፣ እንዲቋረጥብን ያልተደረግን ብቸኛ ነፃ የአፍሪካ ሕዝቦች ስለሆንን... ሁለነገራችን ጥንታዊውን ነገር ያስታውሳቸዋል። ..
የጥንቱን መንፈስ ይቀሰቅስባቸዋል። እንደነዚህ ሪሰርቸሮች፣ ቀና ልብ ያላቸው ይወዱታል። ይፈልጉታል። በአልባሌ መጠቅለያ ውስጥ የዋለውን የከበረውን ነገራችንን ያዩታል። አኗኗራችን በሆነ የተቀደሰ ጥንታዊ መንፈስ የተባረከ መሆኑንም ይመሠክሩልናል።
ጥያቄው እኛስ ግን ተቀብለነዋል? የሚለው ነው። እኛስ ያንን ጥንታዊውን የተቀደሰውን እኛነታችንን እንደ ትርፍ አንጀትና እንግዴ ልጅ ቆርጠን ለመጣልና ትውልድ በማይደርስበት ሥፍራ ለመቅበር ነው መከራችንን እየበላን ያለነው? ወይስ continuityያችንን ለመጠበቅ?
የፅላቱ ታማኝ ጠባቂዎች ነን? ወይስ አደራ በላዎች? የተቀደሰች ምድራችንን ጥለን የምንፈረጥጥ? ነፍሳችን የምታቀነቅነው ዜማ ምንድነው?
በገና ዋዜማ ሳይቸግረኝ ይሄን የቅዱስ ፅላቱን መፅሐፍ ገልጬ... ተወስጄ ቀረሁ! ስለኛ ያልተፃፈልን ነገር የለም! ያኮራል! ልብን ይነፋል ኢትዮጵያዊ መሆን! ኪስን ባይነፋም ልብን ይነፋል! በእውነት!
ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን አብዝቶ ይባርክ!
የትውልዶቻችንን ልብ ይጠብቅ!
መልካም የገና በዓል እመኛለሁ!
አበቃሁ!
🙏🏿❤️
© Assaf Hailu
BY ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
Share with your friend now:
tgoop.com/Bookshelf13/6260