tgoop.com/DBUstudent/1657
Last Update:
🎓🎉 መልካም የምረቃት ቀን ለሁሉም የ2017 ዓ.ም ተመራቂዎች 🎉🎓
ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
ውድ ተመራቂዎች
በቅድሚያ እንኳን ለዚች ለምትናፍቋት እና በጉጉት ስትጠብቋት ለነበረችው ውድ ቀን በሰላም አደረሳችሁ።
ዛሬ የደስታ እና ድል አንድ ቀናችሁ ነው። ከብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችና ዓመታት እንዲሁም ከሌሎች ብዙ አስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረድ በኋላ በመጨረሻም ከዛሬው እለት ደርሳችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።
እናንተ ማለት ለበተሰቦቻችሁ ብርሃን፣ ላሳደጋችሁ እና ላኖራችሁ ማህበረሰብ ተስፋ እንዲሁም ለሃገራችሁ የወደፊት ተረካቢ ናችሁ፤ ይህንንም ደግሞ እስከዛረዋ እለት ድረስ በዘለቀው ጥረታችሁ አረጋግጣችኋልናልና ከልብ እናመሰግናለን።
📚 ከመጀመሪያው ወደ ግቢ ከገባችሁበት እለት እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ያሉት እያንዳዷ እርምጃ በሁላችሁም ህይወት ውስጥ መቼም የማይፋቅ ትውስታ፣ ጓደኝነት እና ቤተሰባዊነትን ጥለው አልፈዋል።
ሁሉም መጨረሻ ለሌላ አዲስ መዕራፍ መጀመሪያ ነውና ይህም ምርቃት ለሌላ አዲስ ተለዕኮ መጀመሪያ ነው ከዚህ ግቢም ወጥታችሁ ቤተሰባችሁንና ሃገራችሁን የምትጠቅሙና ስራ ፈጣሪዎች ሆናችሁ ለሌሎች የምትተርፉ ጥሩና መልካም ዜጋ እንድትሆኑ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፤እንኳንቭተመርቃችሁ!!!
BY DBU የተማሪዎች ህብረት!!

Share with your friend now:
tgoop.com/DBUstudent/1657