tgoop.com/DIYAKONAE/3760
Last Update:
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#መዝ. 86፥1
“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮችናቸው”
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም በእመቤታችን ልደት ምክንያትዛሬ ደስ ሆነ፡፡
በግንቦት 1 ቀን 5ሺ ከ5መቶ የመከራው ዘመን ሊያልቅ 15 ዓመታት ሲቀሩት/ ሊባኖስ በሚባል ተራራ ከፀሐይ የምታበራ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡
ይህቺውም ፍጥረት ሁሉ ደቂቀ አዳም ሁላቸው ተስፋ ሲያደርጓትና ሲጠባበቋት የነበረች የድኅነታቸው ምልክት እመቤታችን ናት፡፡
ሶሪያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም
“አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኀኒትነ፡፡ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል:- የመመኪያችን ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት በድንግል ማርያም ሆነልን” በማለት መናገሩ ስለዚህ ነው፡፡
አክሊል ምክሐነ አላት ይህም አክሊል የወዲህኛው፣ ምክሕ የወዲያኛው ነው። ከነገሥታት መካከል እንደ ዳዊት የከበረ የለም።
ምንም እንኳን ቅዱስ ዳዊት የከበረ ቢሆን የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም፡፡
ወቀዳሚተ መድኀኒትነ አላት፡- ቀዳሚተ የወዲህኛው መድኀኒት የወዲያኛው ነው፡፡ከመሳፍንት ወገን የሚሆን ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢሆን የደኅንነታ መሆን አልተቻለውም፡፡
ወመሠረተ ንጽሕነ አላት:- መሠረት የወዲህኛው፤ ንጽሕ የወዲያኛው ከነቢያተ እግዚአብሔር ወገን የሚሆን ኤልያስ በድንግልና በንጽሕና መኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡
ነገር ግን ምንም ንጹሕ ድንግል ቢባል የንጽሕናችንመሠረት መሆን አልተቻለው።
የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፤ የንጽሕናችን መሠረት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፤” በማለት ተናግሯል።
በእርሷ ምክንያትነት መድኀኒዓለም የሚፈጽምልንን ካሳነቢያትና የቀደሙ አበው ሁሉ
የእርሷን መወለድ በናፍቆት ሲጠባበቁ ነበር።
ከነቢያት አንዱ የሆነ ኢሳይያስም
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርዘርን ባያስቀርልን
ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ጎሞራም በመሰልነ ነበር፡፡” በማለት መናገሩ በእርሷ መገኘት ከጥፋት መዳናችንን ሲገልጽ ነው፡፡
#ኢሳ 1፥9
የቦንጋ ፈ/ሕ/አቡነ ተክለሃይማኖት የበገና ት/ቤት ትምህርት ክፍል ።
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
BY ትምህርተ ኦርቶዶክስ
Share with your friend now:
tgoop.com/DIYAKONAE/3760