tgoop.com/DIYAKONAE/3779
Last Update:
የተቀደደ ልብስ መልበስ
።።።.።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን " የለምጽ ደዌ
ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥.....ርኩስ
ርኩስ ነኝ ይበል።"(ኦሪ ዘሌ.13፥45) እንደሚል
የተቀደደ ልብስ ያለበሰ ሰው የተዋረደና
በኃጢአት እንደረከሰ እርኩስ ነኝ እያለን ነው
ማለት ነው ። ለዚህም ሌላ ማስረጃ የቅዱስ
ዳዊት ልጅ ትእማር በወንድማ በተደፈረች ጊዜ "
ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ
ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም
በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች። ነው
እሚለን (1ኛሳ.13፥19)
ከእስራኤል ወገን በሆነው በአካን ምክንያት
እሥራኤል በደረሰባቸው መከራ ምክንያት "
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ ......"እንዲል መጽሐፍ
ቅዱስ። ( ኢያሱ 7፥6) እኛም የተቀዳደደ ልብስ
ስንለብስ እንደረከስንና በኃጢአታችን መከራ
እየደረሰብን እየገለጽን ነው። እንዲያም ቢሆን
ደግሞ ማቅ ለብሰን አመድ ነስንሰን በንስሃና
በጸሎት ልንበረታ እንጂ ደረታችንን ነፍተን
ባልዘነጥንበት ነበር።
ሌላው መጽሐፍ ቅዱስ በሐዘን ምክንያት
ልብሳቸውን የቀደዱና ያዘኑ እንዳሉ" ያዕቆብም
ልብሱን ቀደደ፥ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ
ብዙ ቀን አለቀሰ።" ሲል አባታችን ያዕቆብ
በዮሴፍ ምክንያት ያለቀሰውን ለቅሶ ጽፎልናል
(ኦሪ.ዘፍ 37÷34) እንዲህ አይነቱን ሐዘን
እዮብም አድርጎታል። " ኢዮብም ተነሣ
መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ....."(ኢዮ.1÷20)
ሰለዚህ ክርስቲያን የተቀደደን ልብስ ሊለብስ
አይገባም በተለይ በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ
ውስጥ ስንገባ እንዲህ አይነት አለባበሶችን
መልበስ ነውር ነው። ገላን እያሳዩ ወደ
ቤተክርስቲያን መግባት ለቤተክርስቲያን ያለንን
ንቀት ከማሳየት ያለፈ ሌላ ትርጉም የለውም።
ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ የአለባበስ
ሥርዓት አላትና።
BY ትምህርተ ኦርቶዶክስ
Share with your friend now:
tgoop.com/DIYAKONAE/3779