tgoop.com/Dengel_Orthopedic_Instruments/1723
Last Update:
ህፃናት እስከ 6 ወር ዕድሜ የእናት ጡት ወተት ብቻ መመገብ እንዳለባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ይመክራል፡፡ ከ6 ወር ጀምሮ ሌላ ተጨማሪ ምግብና የእናት ጡት ወትት እስከ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ መቀጠል እንዳለበትም ይገልፃል፡፡ ከ6 ወር እድሜ ጀምሮ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አስፈላጊ የሆነው የእናት ጡት ወተት ብቻውን ለህፃናት የምግብ ፍላጎት በቂ ስላልሆነ ነው፡፡ ለመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የእናት ጡት ወትት ብቻ መመገብ ሲባል ሌላ ምንም ዓይነት መግብና ውሃን ጨምሮ በሐኪም ካልታዘዘ በቀር መውሰድ የለባቸውም ማለት ነው፡፡
የእናት ጡት ባለማጥባት ወይም ለመጀመሪያ 6 ወር ጡት ብቻ ባለማጥባት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት 1.4 ሚሊዮን ሞት እና 10 ከመቶ (10%) ያህሉ በሽታዎች ከ5 አመት በታች ባሉ ህፃናት ላይ ይከሰታሉ፡፡
👍የእናት ጡት ወተት/ጡት ማጥባት ለህፃናት ያለው ጥቅም
🟢 የህፃናትን ሁለንተናዊ እድገት (አካላዊና አዕምሯዊ እድገት) ያፋጥናል፣
🟢 ሁልጊዜ ንፁህና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፣
🟢 የህፃናት ሰውነት ራሱን ከበሽታ እንዲከላከል የሚያግዝ ይዘት አለው (የክትባት ባህሪ ያላቸው ንጥረ ነገሮች አሉት)፣
🟢 በቀላሉ መፈጨት በመቻሉ በውስጡ ያሉ ንጥረ-ነገሮች በቀላሉ ሰውነት ውስጥ መንሸራሸር ይችላሉ፣
🟢 የህፃናት ሰውነት የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ይይዛል (እስከ 87 ከመቶ (87%))፣
🟢 የአፍና የፊት ጡንቻዎችን ዕድገት ያፋጥናል ወይም ቶሎ እንዲጠነክሩ ያደርጋል፣
🟢 የእናትና ልጅ ትስስርን ወይም ፍቅርን ያጠናክራል፣
🟢 እስከ 6 ወር ዕድሜ ሁሉን ያቀፈ ምግብ መሆን ይችላል፤ ማለትም ምንም አይነት ተጨማሪ ምግብ አያስፈልግም፣
🟢የመጀመሪያው የእናት ጡት ወተት (እንገር) ሆድ የማለስለስ ባህሪ ስላለው ህፃናት የሆድ ድርቀት እንዳይገጥማቸው ይከላከላል፡፡
👍 ጡት ማጥባት ለእናት ያለው ጥቅም
🟢 ለመጀመሪያ 6 ወር እርግዝና እንዳይከስት ይከላከላል፤ ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው እናትየው የወር አበባ ማየት እስካልጀመረች ድረስ ብቻ ነው፤
🟢 የእንግዴ ልጅ አንዲወጣ/እንዲወርድ ያፋጥናል፣
🟢 ከወሊድ በኋላ የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል፣
🟢 ቶሎ ጡት ማጥባት መጀመር ቀጣይነት ያለው በቂ የሆነ ወተት ምርት እንዲኖር ያስችላል፣
🟢 የጡት መወጠር እንዳይኖር በማድረግ ከርሱ ጋር ተጓዳኝ የሆኑ ችግሮች እንዳይከሰቱ ይከላከላል፣
🟢 እንደምግብ ማዘጋጀት፣ ህፃኑ/ኗን ማስቀመጥና መመገብ የመሳሰሉ የስራ ጫናዎችን ይቀንሳል፡፡
BY ደንገል የጤና ትራሶች
Share with your friend now:
tgoop.com/Dengel_Orthopedic_Instruments/1723