tgoop.com/Dengel_Orthopedic_Instruments/1854
Last Update:
- ፀሐይ ስታሞቂ ምንም ነገር አትቀቢው፣ ምክንያቱን የምቀቢው ቅባት ወይም ቅቤ ቆዳው ላይ መድረስ ያለበትን ብርሃን (ጨረር) እንዳይደርስ ያደርገዋል።
- ለረጅም ፀሐይ የማይገኝበት ወቅት እና ቦታ ላይ ከሆንሽ ሐኪምሽን ማማከር ይኖርብሻል !!
ማስጠንቀቂያ !
- የፀሐይ ብርሃን ያላገኙ ልጆች የአጥንት መልፈስፈስ እና መጣመም አልፎ አልፎም መሰበር ያጋጥማቸዋል፣
- ልጅሽ አንድ አመት እስከሚሞላ ፀሀይ ማሞቅ ይኖርብሻል፣
4. ለእትብቱ አስፈላጊ የሆነውን ጥንቃቄ ማድረግ:-
- የህፃናት እትብት ብዙ ጊዜ የሚወድቀው እስከ 2 ሳምንት ባለው ጊዜ ነው ሆኖም ከ3 ሳምንት በላይ ሳይወድቅ ከቆየ ሐኪም ማየት ይኖርበታል፣
- እትብቱ እስኪወድቅ ድረስ በንጹህ ጥጥ ወይም ጋቢ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ እየነከሩ ሰውነቱን ማፅዳት፣
- እትብቱ ቶሎ እንዲወድቅ እትብቱ አካባቢ ንፁህ እና ደረቅ ሆኖ መቆየት አለበት ሆኖም መቅላት ካለው ወይም ሽታ ያለው እንደ መግል አይነት ፈሳሽ ወይም ደም ካለው ለሐኪም ማሳየት ይገባል።
5. ዳይፐር አጠቃቀም:-
- ዳይፐሩን በአግባቡ (በቀን 4-6 ጊዜ ) እና እንደ አስፈላጊነቱ መቀየር።
- ዳይፐር ከማድረግሽ በፊት የልጅሽ ቆዳ ቀስ ብለሽ አጽጅው ከዚያም እንዳይላጥ ወይም ሽፍታ እንዳይወጣበት ዳይፐር የሚያርፍበት ቦታ ላይ በስሱ ቫዝሊን ቀቢው።
- ለልጅሽ የሚሆነውን ቁጥርና የሚስማማውን አይነት ምረጭ።
- ዳይፐር ለማድረግ በጎን በኩል ገልበጥ አድርገሽ እንጅ ከታች ወደ ላይ አታንሽው፣
6. ገላውን ማጠብ:-
- ጨቅላ ህፃንን ማጠብ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
- እንዳያሟልጭሽ እና አይኑና አፍንጫው ውስጥ ሳሙና እንዳይገባ በጥንቃቄ እጠቢው።
- በተለይ የመጀመሪያሽ ከሆነ ለሁለት ሆኖ ማጠቡ የተሻለ ነው።
7. የቆዳ እንክብካቤ:-
- የልጅሽን ሙሉ ቆዳውን ለህፃናት በተዘጋጁ ቅባቶች ማለስለስ ይኖርብሻል።
- በዚያውም ሰውነቱን ማሳጅ ማድረግ ጡንቻዎቹን ያነቃቃቸዋል።
8. ክትባቱን በሰዓቱ አስከትቢ:-
- ለህፃናት ጤና ክትባት በጣም ወሳኝ ነገር ነው ስለዚህ ሁሉንም ክትባት በቀጠሮ አስከትቢ፣
9. የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም ጋር ክትትል አድርጊ !!
ከላይ ያላየናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ በተለይ ልጅሽ ላይ ለየት ያለ ነገር ካየሽ ሀኪምሺን አማክሪ።
አዘጋጅ (Prepared by) :-
👇
ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ፣ የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፌሰር )
BY ደንገል የጤና ትራሶች

Share with your friend now:
tgoop.com/Dengel_Orthopedic_Instruments/1854