tgoop.com/Dnabel/1627
Last Update:
+++ ያለ እግዚአብሔር "እንደ እግዚአብሔር" +++
በእባብ ሥጋ ተሰውሮ ወደ ሔዋን የመጣው ሰይጣን ሴቲቱን ያታለለበት የሐሰት ቃል "ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው" የሚል ነበር።(ዘፍ 3፥5) ይገርማል! በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረ የሰው ልጅ እንደ እግዚአብሔር (እርሱን መስሎ) የመኖር ፍላጎት እንዳለው ሰይጣን ያውቃል። ይህ ውሳጣዊ ፍላጎቱ ላይ ለመድረስ በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ከማደግ ይልቅ ባልተገባ መንገድ ፍለጋውን ያደርግ ዘንድ አዲስ ስብከት አመጣለት። ምን የሚል? "ያለ እግዚአብሔር 'እንደ እግዚአብሔር' ትሆናላችሁ" የሚል። በምን? በቅጠል።
ዛሬም ሰይጣን ያለ እግዚአብሔር "እንደ እግዚአብሔር" ትሆኑባችኋላችሁ ሲል የሚያሳየን እንደ ገንዘብ፣ ዕውቀት፣ ጉልበት ያሉ ብዙ ቅጠሎች አሉ። ነገር ግን እኛ ክርስቲያኖች እርሱን ወደ መምሰል የምናድግበት ብቸኛው መሰላላችን ረድኤተ እግዚአብሔርና የማይቋረጥ የእኛ ሩጫ ነው። እርሱ ሳይኖር እና ሳያካፍል እኛ በራሳችን የምንካፈለው ምንም አምላካዊ ምሳሌነት የለም።(2ኛ ጴጥ 1፥4)
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tgoop.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
BY Dn Abel Kassahun Mekuria

Share with your friend now:
tgoop.com/Dnabel/1627