tgoop.com/Dnabel/1637
Last Update:
ላትሞት ነው የምትፈታው?
(የሆሣዕና ፍትሐት)
ቤተ ክርስቲያናችን በበዓለ ሆሣዕና ቀን ከምታከናውናቸው ነገሮች መካከል አንዱ ለክርስተኢያኖች ሁሉ ፍትሐት ማድረግ ነው። ይኸውም ከሆሳዕና ቀጥሎ ባሉት ቀናት ሌሎቹን አገልግሎት ሁሉ ለጊዜው አቁማ ልክ እንደ ሰጎን ዕንቁላል ከክርስቶስ ሕማም እና ሞት ላይ ዓይኗን ስለማታነሣ፣ በዚህ ሳምንት የሚያንቀላፋ ቢኖሩ ቀድማ በዕለተ ሆሳዕና ፍትሐት ታደርግለታለች።
ይሁን እንጂ የፍትሐቱ ዋናው ምሥጢር ያለው ግን እዚህ ላይ ነው። ክርስቶስ የተቀበለው መከራ እና ሞቱ በሚታሰብበት በመጪው ሳምንት ልጆቿ ምእመናን የሥጋ ፈቃዳቸውን በመስቀል ሰቅለው ስለ እነርሱ ሲል ለሞተው አምላክ፣ እነርሱም ለዚህ ዓለም ፍትወት የሞቱ ሆነው እንዲያሳልፉ ለማሳሰብ ነው። ስለዚህም ክርስቲያኖችን ሁሉ በቁማቸው ሳሉ እንደ መነኮሳቱ (ለዓለሙ ፈቃድ እንደ ሞቱት) ፍትሐት ታደርግላቸዋለች። ታዲያ በሆሣዕና ሰንበት ወደ ቤተ ክርስቲያን ለፍትሐት ስትመጣ ለራስህ ፈቃድ ሙት ሆነህ ለክርስቶስ ለመኖር ወስነህ ነው? ወይስ ላትሞት ነው ለመፈታት የምትሄደው?
“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ”
2ኛ ቆሮ 5:15
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tgoop.com/Dnabel
BY Dn Abel Kassahun Mekuria

Share with your friend now:
tgoop.com/Dnabel/1637