tgoop.com/DrYonasLakew/2584
Last Update:
ትውስታ እና የህግ ምስክርነት
===================
ትውስታ ባይኖር ህይወታችን የተለየ መልክ ይኖረው ነበር። ለምሳሌ ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ ትውስታ ባይኖረን ቤት ውስጥ የምናገኘውን ሰው "ምን እያደረግህ ነው፣ ከየት ነው የመጣኸው፤ እና በዋናነት ደግሞ ማነህ?" ልንል እንችላለን። ትውስታ ትናንት እና ነገአችንን የሚያገናኝ ድልድይ ነው። ትውስታ ባይኖር ጓደኝነት አይታሰብም።
ትውስታችን የሚያጋጥመንን ነገር ሁሉ 'ሴቭ' ቢያደርግ ቦታ ስለሚሞላ ወይም ለመለየት አስቸጋሪ ስለሚሆን ስሜት ያልተጫነባቸውን ክስተቶች ላሽ ይላቸዋል። አምስተኛ ክፍል እያለን አንድ አርብ ክለባችን አየር ሀይል ምድር ባቡር ከተባለው ሌላ ክለብ ጋር ተጫውቶ ዋንጫ በልቶ ነበር። ጨዋታው ላይ በረኛችን አንድ ኳስ ተወርውሮ ሲይዝ እንዲሁም ነውጠኛው የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች ተቀይሮ ሲገባ ቁልጭ ብሎ አሁንም ትዝ ይለኛል። አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሀሙስ እለት በትምህርት ብቻ ነበር ያለፈው። ማን እንዳስተማረን፣ ምን እንደተማርን የማስታውሰው ዜሮ ነው።
የአይን ምስክር ተብለው ፍርድ ቤት ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ሳያውቁ በስህተት፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አውቀው በድፍረት ትውስታቸው የተሳሳተ ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። በቀጣይ ምሳሌዎችን አቀርባለሁ። ለዛሬው ግን ሮጀር ሚላ የኮርና እንጨቷ ጋር ሄዶ በአንድ እጁ ወገቡን ይዞ እንደ ያንቡሌ የጨፈረውን እናስታውሳለን። ጎሏን የምናስታውስ ስንቶች እንሆን። በተመሳሳይ ረሺድ ያኪኒ መረቡን ይዞ ያለቀሰ ጊዜ ኳሱን ያቀበለው ማን ነበረ?
በዩቲዩብ ተቀላቀሉ https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
BY Mental wellness የአእምሮ ጤና
Share with your friend now:
tgoop.com/DrYonasLakew/2584