DRYONASLAKEW Telegram 2653
ከአእምሮ ህክምና ጋር የተያያዙ ትክክል ያልሆኑ ግምቶች
==============================
የአእምሮ ሀኪም ጋር ሲኬድ ምንድነው የሚያጋጥመው? አንዳንድ ሰዎች ምን እንደሚጠብቁ ስለማያውቁ ለመሄድ ያመነታሉ፡፡ ከአእምሮ ህክምና ጋር ተያይዞ የሚነሱ የተሳሳቱ ግምቶች፦

የአእምሮ ህክምና ራሱን ለማያውቅ ሰው ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች በጓደኞቻቸው፣ በቤተሰብ ወይም በሀኪም የአእምሮ ህክምና እንዲያደርጉ ሲመከሩ ደስተኛ አይሆኑም፡፡ "እኔ ራሴን አውቃለሁ፡፡" ይላሉ፡፡ ከባድ የአእምሮ መረበሽ ያለባቸው ሰዎች ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡ ነገር ግን የአእምሮ ህክምና ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የስራ ጫና ያለባቸው፣ የልጅ አስተዳደግ የሚያስጨንቃቸው፣ ትዳራቸው/የፍቅር ህይወታቸው የሚያሳስባቸው...ወዘተ ናቸው፡፡

የአእምሮ ሀኪሞች አእምሮ ያነብባሉ፡፡

የአእምሮ ሀኪም አእምሮ የሚያነብ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ "ይሀው መጥቻለው አንብቡና መድሀኒት ስጡኝ" አይነት አቋም ይዘዉ የሚመጡ ፡፡ የዚህ አይነት ግምት ምንጩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ህክምናዎች ናቸው፡፡ አእምሮ አናነብም!! ታካሚን ለመረዳትና ለመርዳት የሚሰማውንና የሚያስበውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ጥያቄዎች ልንጠይቅ እንችላለን ሆኖም ታካሚዎች ምቾት የማይሰጣቸው ከሆነ ያለመመለስ ፍላጎታቸውን እናከብራለን፡፡ በተጨማሪም ራስን ወይም ሌላን ሰው ስለመጉዳት ካልሆነ በቀር የምንነጋገራቸው ነገሮች በሀኪም እና በታካሚ መሀከል የሚጠበቅ ሚስጥር ነው፡፡

የኔን አይነት ነገርማ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡

አንዳንድ ሰዎች ያጋጠማቸው ሁኔታ ወይም የሚያስቡት ሀሳብ የሚከብድ ነው ብለው ሲገምቱ ተረካቸውን ለማስተካከል ይሞክራሉ፡፡ ሁሉም ሰው የየራሱ ታሪክ ቢኖረውም ተመሳሳይ ነገር ውስጥ ያለፉ ሰዎች ታሪክ ከመፅሀፍት ወይም በስራቸን ያጋጥመናል፡፡የምንሰማው ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ የምንሰማው አይሆንም፡፡ ሰዎች ስለ አእምሮ ህመምም ሆነ ስለህክምናው መድልዖ እና መገለልን በመፍራት እርስበርስ አያወሩም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ከአለም ተነጥሎ ብቻውን አየታመመ ያለ ይመስለዋል፡፡

በአጠቃላይ አብዛኞቹ የአእምሮ ህመሞች ሰዎች በጊዜ ህክምና ካገኙ ጥሩ ውጤት ይኖራቸዋል፡፡ ነገር ግን በተሳሳተ ግምት ምክኒያት ሰዎች አስፈላጊውን ህክምና ህመሙ ቀላል እያለ ሳያገኙ ይቀራሉ። ስለ አእምሮ ህክምና ግንዛቤ እንዲስፋፋ የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል።

በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

tgoop.com/DrYonasLakew/2653
Create:
Last Update:

BY Mental wellness የአእምሮ ጤና

Share with your friend now:
tgoop.com/DrYonasLakew/2653

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

6How to manage your Telegram channel? Hui said the time period and nature of some offences “overlapped” and thus their prison terms could be served concurrently. The judge ordered Ng to be jailed for a total of six years and six months. The Standard Channel The Channel name and bio must be no more than 255 characters long Telegram channels fall into two types:
from us

Telegram Mental wellness የአእምሮ ጤና
FROM American