tgoop.com/DrYonasLakew/2688
Last Update:
ዳንኤል አጥላባቸው የልጅነት ጓደኛዬ ነው። በጣም ቅን አሳቢና ፀባየ ሸጋ ነው። ዳኒ የዛሬ አንድ አመት ተኩል አኪዩት ማዬሎይድ ሉኬሚያ (Acute myeloid leukemia) የተባለ የደም ካንሰር እንዳለበት ተነገረው። ህክምናው ኢትዮጲያ ስለሌለ በእናንተ እገዛ ህንድ ሀገር ሄዶ የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ አድርጎ ደህና ሆኖ ተመለሰ።
የመቅኔ ንቅለ ተከላው እጅግ ከባድ ነበር። ለተወሰኑ ቀናት የህክምና ክፍሉ ውስጥ ከሀኪም በስተቀር ሰው አይገባም ነበር። ለቀናት ምግብ ሳይበላ በግሉኮስ ብቻ ነበር የቆየው። የኬሞቴራፒ መድሀኒቶቹ ቀጣም ከባድ ናቸው። ዳኒ በዛ ሁሉ ህመም ፣ በዛ ሁሉ ብቸኝነት፣ በዛ ሁሉ አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ሆኖ ሁሌ በፈገግታ "እግዚአብሄር ይረዳኛል። አሁን እኮ ደህና ነኝ።" ነበር የሚለው። ጥንካሬውና እምነቱ ይገርመኛል።
ዳኒ ህክምናውን ከተከታተለ በኋላ ጤንነቱ ጥሩ ነበር። የዛሬ ስድስት ወር በስልክ ስናወራ "አሁን በዛ ከባድ ጊዜ ሁሉ አጠገቤ ከነበረችው እጮኛዬ ትንሳኤ ጋር እግዚአብሄር ቢፈቅድ ስለሰርግ እያሰብን ነው። እገዛ ላደረጉልኝ ሰዎችም ምስጋናዬን ፖስት አድርግልኝ።" ብሎኝ ፖስት አድርጌለት ነበር።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዳኒ የአጥንት ህመም ይሰማው ጀመረ። ምርመራዎች ከተደረጉለት በኋላ ካንሰሩ እንዳገረሸ ተነገረው። ዳኒ በሁኔታው ቢደናገጥም አሁንም በእግዚአብሄር ላይ ያለው እምነት ፅኑ ነው።
ሀኪሞች ሁለተኛ ዙር የመቅኔ ንቀለ ተከላ እንዲደረግለት ወስነዋል። እህቱም በድጋሚ ልትሰጠው ዝግጁ ናት። ለህክምናው 110 ሺ USD ያስፈልገዋል። ሁላችንም በንግድ ባንክ አካውንቱ ወይም በGofundme የምንችለውን እናስገባ። ዳኒ ያጋጠመውን የህይወት ፈተና ለመጋፈጥ በእምነትና በተስፋ ቆሟል። ሁላችንም የምንችለውን እናግዘው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዳንኤል አጥላባቸው
1000289986107
Support Daniel Atlabachew's Second Transplant
https://gofund.me/64cfcc91
ሼር፤ሼር፣ሼር!!!
BY Mental wellness የአእምሮ ጤና
Share with your friend now:
tgoop.com/DrYonasLakew/2688