tgoop.com/DrYonasLakew/2694
Create:
Last Update:
Last Update:
ማን ነው የተረዳው (ቁ.3)
የረገጥከው መሬት ያለፍከው መከራ
ቀላል አይባልም እንዲሁ የሚወራ
ጦር ካቆሰለው አካሉን ከጎዳው
የውስጥህን ሕመም ማን ነው የተረዳው?
የትላንት መካሪ አለው የምትል ለሰው
አጣሁኝን ማታውቅ ለሁሉ የምትደርሰው
ተረተህ እጅ ብትሰጥ ጊዜ ጣለህና
ወዳጆችህ ራቁ መሳትክን አዩና
እርግጠኛ ሆነው በእነርሱ ጤንነት
በአንተ መንገዳገድ ስምህን ቀየሩት
በሕመም ላይ ሕመም እየጨማመሩ
ባገኙት አጋጣሚ ሊያጠፉህ መከሩ
ወንድ ነው በማለት ሊረዳህ አልሞከረ
በተሳሳተ እሳቤ ስንቱ ከቤት ቀረ
ፆታን መሰረት አድርገው ምኑም ሳይገባቸው
ብዙዎችን አጣን ቀርበን ሳንረዳቸው
ሊያበረቱህ ሲቻል ሕመምክን አባሱ
እርግማን አድርገው ሲገፉህ ሲያንኳሱ
ቡቱቶህን አይተው ሊያዩህ ተጠየፉ
ፊታቸውን አጥቁረው ተረማምደው አለፉ
መጨረሻው ይህነው ወንድ ሆኖ መታመም?
አዎ...በእኛ ማህበረሰብ የሚረዳህ የለም
እናም ተስፋ አትቁረጥ ፈልግ ራስህን
በሌላ የተኩትን ቀይረው ስምህን።
ናትናኤል ኃይሌ
BY Mental wellness የአእምሮ ጤና
Share with your friend now:
tgoop.com/DrYonasLakew/2694