tgoop.com/Dreyob/3619
Last Update:
የራእይ ጉልበት
በሕይወታችሁ በፍጹም መፍትሄ ሊያገኙ እንደማይች እስከሚመስላችሁ ድረስ የሚመጡ ፈተናዎችና ችግሮች አሉ?
እነዚህ ፈተናዎችና ችግሮች ብዙ ነገር ሞክራችሁ እንኳና ልባችሁን ከመጎተትና ተስፋ ከማስቆረጥ ላያባሩ ይችላሉ፡፡ ለእንደዚህ አይነቶች ከባድ ፈተናዎች መፍትሄ እንዲሆን ፈጣሪ የሰጣችሁ ታላቁ ስጦታ የራእይ ስጦታ ነው፡፡
ለተለያዩ ችሮች የተለያዩ የመፍትሄ አማራጮችን የመውሰዳችሁ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለሁሉም ነገር መነሻ የሆነው ራእያችሁን የማወቅና የመከታተል ጉዳይ እጅጉን ሊታሰብበት ይገባል፡፡
• ከዚህ በፊት በሰራችሁት ስህተትና በወሰናችሁት አጉል ውሳኔ ምክንያት ጸጸት ውስጥ ካላችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱ ላይ ማተኮር ትጀምራላችሁ፡፡
• ሕይወታችሁን ሁሉ ሰጥታችሁት ሳለ ትቷችሁ የሄደ ወዳጅ፣ ጓደኛ፣ ፍቅረኛ ወይም የትዳር አጋር ሁኔታ እጅጉን ከጎዳችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ሕይወታችሁ በአንድ እናንተን ባልፈለገ ሰው ላይ ብቻ ከመንጠልጠል ይላቀቅና ራሳችሁን መምራትና ማሻሻል ትጀምራላችሁ፡፡
• ያላችሁበት የኑሮ ደረጃ በጣም የሚያታግልና ከባድ ከሆነባችሁና በዚሁ ሁኔታ እስከወዲያኛው እንደምትቀጥሉ እያሰባችሁ ከሰጋችሁ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ የዛሬውን ኑሯችሁን አልፋችሁ የተሻለ የወደፊት ውስጥ እንደምትገቡ ተስፋን ትጨብጣላችሁ፡፡
• በሆነ ባልሆነው የሚናወጥ ስሜትና ተስፋ-ቢስነት የሚያጠቃችሁ ከሆነ . . . ራእያችሁን ስትለዩና መከተል ስትጀምሩ ውስጣችሁ ራእያችሁን በማሰብ፣ ስለእሱ በማቀድና ወደ ተግባር በመግባት ስለሚሞላ ለተስፋ ለመቁረጥ ጊዜም አይሰጣችሁም፡፡
ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላችሁም የተፈጠራችሁለትን ራእያችሁን ለማወቅ ጊዜን ውሰዱ! ራሳችሁን አሰልጥኑ! እሱን ተከታተሉ! መላውን ካላወቃችሁበት አጋዥ አግኙ!
ይህንን በማድረግ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ተመልከቱ!
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
BY Dr. Eyob Mamo
Share with your friend now:
tgoop.com/Dreyob/3619