DREYOB Telegram 6026
ለጥቂት ቀናት ሸክምን አስመልክቶ አንዳንድ መሰረታዊ ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡

መሸከም የሌለብህ ሸክሞች (ክፍል አንድ)
የኑሮ ሸክም ሲከብደን የሚታዩ ምልክቶች

ዙሪያችንን በሚገባ ብንቃኘው፣ የኑሮ ሸክም ከብዷቸው የሚንገዳገዱና ደፋ ቀና የሚሉ ብዙ ሰዎች እናያለን፡፡ ምናልባትም ይህ ጉዳይ እኛንው ይመለከተን ይሆናል፡፡

ማንኛውም ሰው ወደዚህች ምድር በፈጣሪው ፈቃድ ሲመጣ ኑሮውን ለመግፋትም ሆነ ላለው ማሕበራዊ ሃላፊነት በቂ የሆነን ጉልበት ተቀብሎ ነው የሚመጣው፡፡ እንደዚያ የማይሰማን ጊዜ ግን ጥቂት አይደለም፡፡

ብዙ ሰው የኑሮው ሂደት ሲከብደውና ወደ ፊት መራመድ ሲያቅተው ራሱን ያገኘዋል፡፡ ይህ ከሚሆንበት ምክንያት አንዱ መሸከም የማይገባውን ሸከም ሲሸከም ነው፡፡

“መሸከም የማይገባን ሸከም ምን ማለት ነው? . . . መሸከም የማይገባን ሸከም ራሳችን ላይ መጫናችንን እንዴት ማወቅ ይቻላል? . . . እንዴትስ ማራገፍና ወደ ቀድሞ አቅማችን መመለስ እንችላለን?”

አንድ ሰው ከልጅነት እድሜዎቹ አልፎ ወደ ወጣትነትና ጎልማሳነት እየዘለቀ በሄደ ቁጥር በጎዳናው ላይ የሚለቃቅማቸው በርካታ የልምምድ “ሻንጣዎች” አሉ፡፡ እነዚህ “ሻንጣዎች” የጓደኝነት፣ የስራ፣ የራእይ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

በአነዚህ “ሻንጣዎች” ውስጥ ብዙ ኮተቶች ይገኛሉ፡፡ የተከናወነውና ያልተከናወነው . . . የተሳካውና ያልተሳካው . . . ያጓጓንና ጉጉታችንን የሰረቀው . . . ታሪኩ ብዙ ነው፡፡

እነዚህን ሸክሞች ከላይ ከላዩ እያራገፍን ካልሄድን ቀስ በቀስ በላያችን ላይ የጫንነው ሸከም ከአቅማችን በብዙ እጥፍ እየገዘፈ ይመጣና እርምጃችንን ይገታዋል፡፡

በርእስ ላይ ምንም ነገር ከመነጋገራችን በፊት የየእለት ኑሮህ ሸክም እንደከበደህ የምታውቅባቸው ዋና ዋና ምልክቶች:-

1. ነገን ለማየትና ለመጋፈጥ ያለህን ጉጉት ማጣት

2. ኑሮህ፣ ስራህ፣ ትምህርትህ ወይም ማሕበራ ግንኙነት የሚፈልግብህ ሁኔታና የአንተ አቅም አልመጣጠን ማለት

3. ቀድሞ ትጓጓባቸው በነበሩ ነገሮች አሁን አለመጓጓት

4. ለአንዳንድ መሰረታዊ ነገሮች አቅም የማጣት ስሜት

5. የተስፋ ቢስነትና የባዶነት ስሜት

6. ከሰዎች ለመለየት የመፈለግ ስሜት

7. የድብርት ስሜትና ከቤት መውጣት አለመፈለግ

8. የአሉታዊ (ጨለምተኛ) ስሜት

9. የጭንቀትና የመረባበሽ ስሜት

10. ደክሞህ እንኳን እንቅልፍ የማጣት ሁኔታ

ከእነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት ሁኔታዎች የተወሰኑት እንዳሉብህ ካሰብክ የኑሮህ ሸክምና ያንን ኑሮ ለመኖር ያለህ አቅምህ አለመመጣጠኑን፣ እንዲሁም ያልተገባህን ሸክም መሸከምህን ጠቋሚ ነው፡፡

ትክክለኛው አቅምህና ማንነትህ አሁን ያለህበት እንዳልሆነ ከተሰማህና በስነ-ልቦናህና በስሜትህ “ጤናማ” በነበርክበት ጊዜ ከዚህ የተሻለ ጉጉትና ግለት እንደነበረህ ከተገነዘብክ የሚቀጥሉትን ትምህርቶች ተከታተላቸው፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

tgoop.com/Dreyob/6026
Create:
Last Update:

BY Dr. Eyob Mamo

Share with your friend now:
tgoop.com/Dreyob/6026

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

End-to-end encryption is an important feature in messaging, as it's the first step in protecting users from surveillance. How to build a private or public channel on Telegram? The SUCK Channel on Telegram, with a message saying some content has been removed by the police. Photo: Telegram screenshot. Click “Save” ;
from us

Telegram Dr. Eyob Mamo
FROM American