tgoop.com/Dreyob/6033
Last Update:
የጸጸቶቻችን ጉዳይ!
ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ በማሰብ ከዚህ በፊት የተጸጸታችሁባቸውን ሁኔታዎች ብታስቡ፣ አብዛኛዎቹ ነገሮች ከስሜታችሁ ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ትደርሱበታላችሁ፡፡
በአንድ በኩል ለሁኔታዎች በስሜታዊነት ምላሽ የሰጣችኋበቸውን ነገሮች ታገኛላችሁ፡፡
ተረጋግታችሁ በማሰብ ምላሽ መስጠት ሲገባችሁ በችኮላ እና ከወቅቱ የስሜት ግልት በመነሳት የተናገራችኋቸው ወይም ያደረጋችኋቸው ነገሮች፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ተገቢ ምላሽ ለሚገባው ነገር ምላሽ ከመስጠት የተከለከላችሁባቸውን ነገሮች ታገኛላችሁ፡፡
ተገቢውን የንግግር ወይም የተግባር ምላሽ መስጠት ሲገባችሁ በወቅቱ ከነበረባችሁ ፍርሃት ወይም ሰውን ለማስከፋት ያለመፈለግ ስሜት የተነሳ ዝም በማለት ምንም የተዋችኋቸው ነገሮች፡፡
አሁን የሚሰማችሁም ሆነ ወደፊት የሚፈጠር አብዛኛው ጸጸት ከእነዚህ ሁለት ሁኔታዎች ይመነጫሉ፡፡
በስሜት ብልህነት መብሰል በአንድ በኩል ለሰዎችና ለሁታዎች የምንሰጣቸውን ምላሾች በሚዛናዊነት እንድንይዝ ያደርገናል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ጊዜ የተፈጠረን የጸጸት ሁኔታ አያያዙን እንድናውቅበትን ከዚያ አልፈን እንድንሄድ ያግዘናል፡፡
ከነገ ወዲያ ኃሙስ የሚጀምረው ስልጠና በስሜት ብልህነት የመብሰልን ተግባራዊ እውነታ በሚገባ ያመላክታችኋልና አያምልጣችሁ፡፡
የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል
@DrEyobmamo
BY Dr. Eyob Mamo
Share with your friend now:
tgoop.com/Dreyob/6033