tgoop.com/Dweyane1967/2326
Last Update:
ለቸኮለ!
የዛሬ ማክሰኞ የካቲት 3/2012 ሲስተጋቡ የዋሉት ዐበይት ዜናዎች
1. በሕዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ላይ የሦስቱ ሀገራት የሕግ እና ቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን አስማሚ የስምምነት ሰነድ ማዘጋጀት እንዳልተቻለ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል፡፡ የውሃ እና ኢነርጅ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ የኮሚቴውን ሰነድ ትናንት ከሱዳን እና ግብጽ አቻዎቻቸው ጋር ገምግመዋል፡፡ ውይይቱ ዛሬ ይቀጥላል፡፡
2. ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል እንዳቋቋመች የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማስታወቁን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ ማዕከሉ የደም ናሙናን ወደ ደቡብ አፍሪካ መላክን ያስቀራል፡፡ በቫይረሱ ተጠርጥረው ማዕከል የገቡ በሙሉ ነጻ ሆነው ወጥተዋል፡፡
3. 398 ቤተ እስራዔላዊያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራዔል እንዲጓጓዙ የእስራዔል ካቢኔ እንደፈቀደ እየሩሳሌም ፖስት ዘግቧል፡፡ ሰዎቹ ከ2 ዐመት በፊት መጓጓዝ የነበረባቸው ናቸው፡፡ ባሁኑ ሰዓት በእስራዔል ቤተሰብ ያላቸው 8 ሺህ ቤተ እስራዔላዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለጉዞ ጥበቃ ላይ ናቸው፡፡
4. በሐሰተኛ የጉዞ ሰነዶች ዜጎችን ውጭ ሀገር የላኩ ግለሰቦች በ10 ዐመት ጽኑ እስራት እንደተቀጡ ሸገር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ግለሰቦቹ ሥራ ፈላጊ ዜጎችን ውጭ የመላክ ፍቃድ ሳይኖራቸው ከእያንዳንዳቸው 60 ሺህ ብር በመቀበል ወደ ሳዑዲ ልከዋል፡፡ በሐሰተኛ ሰነድ የተላኩ ዜጎች በፖሊስ ተይዘው ወደ ሀገር ተመልሰዋል፡፡
5. በምስራቅ አፍሪካ ለጸረ አንበጣ መድሃኒት ርጭት ተመድ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ሊያሰማራ እንደሆነ ሪሊፍ ኤይድ ድረገጽ ዘግቧል፡፡ ለድሮኖቹ የተገጠመው ቴክኖሎጅ አንበጣ መንጋ ያለበትን ቦታ በቀላሉ ይለያል፤ ድሮኖቹም የበረራ ፍጥነታቸውን እና ከፍታቸውን እንዲስተካክሉ ያስችላል፡፡ ካሁን በፊት ድሮን ለመድሃኒት ርጭት ተሞክሮ አያውቅም፡፡
6. ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሐሙስ አስቸኳይ ስብሰባ እንደተጠራ ምክር ቤቱ በፌስቡክ ገጹ ካሰራጨው መረጃ ተረድተናል፡፡ አወዛጋቢዎቹ የኤክሳይስ ታክስ እና የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ረቂቂ አዋጆችን እንዲያጸድቅ ይቀርቡለታል፡፡
7. የሱዳን ሽግግር መንግሥት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሐሰን አልበሽርን ለዐለም ዐቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት አሳልፎ ለመስጠት እንደወሰነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
@dimtsiweyane1967
@Dweyane1967bot
BY ኣልፋ ጥዕና
Share with your friend now:
tgoop.com/Dweyane1967/2326