tgoop.com/Dweyane1967/2347
Last Update:
ለቸኮለ!
የዛሬ ረቡዕ የካቲት 4/2012 ሲስተጋቡ የዋሉት ዐበይት ዜናዎች
1. ምርጫ ቦርድ ስለ ጃዋር ሞሐመድ የኢትዮጵያ ዜግነት መልሶ ማግኘት ጉዳይ ከኢምግሬሽን ባለሥልጣን ማብራሪያ እንደጠየቀ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡ የተፈለገው ማብራሪያ የውጭ ዜጋ የሆነ ሰው የውጭ ዜግነቱን ትቶ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ እንዲመለስለት ከጠየቀ ወዲያውኑ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይቆጠር እንደሆነ ነው፡፡ ኢምግሬሽን እስከ የካቲት 9 ምላሽ ይስጠኝ ሲል ቦርዱ አመልክቷል፡፡
2. አምና ዕጣ የወጣባቸውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማከፋፈል የፌደራል መንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሆነ ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ቤቶቹ በኦሮሚያ ክልል መሬት ላይ ነው የተሠሩ በሚል ተቃውሞ ማስተላለፉ መጓተቱ ይታወሳል፡፡ ከዕደለኞች እስካሁን አቤቱታ እንዳልቀረበላቸው የከተማው አስተዳደር ቤቶች ልማት ሃላፊ ተናግረዋል፡፡
3. ገለልተኛ የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት እንደተቋቋመ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ አማካሪ ምክር ቤቱ 12 አባላት አሉት፡፡ ምክር ቤቱ የግሉ ዘርፍ በሀገር በቀሉ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መርሃ ግብር አተገባበር ቁልፍ ሚና እንዲጫወት ያግዛል፡፡
4. የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ እና የሱማሌላንድ ራስ ገዝ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚስጢር ፊት ለፊት እንደተገናኙ ኒውዮርክ ታይምስ የሱማሊያውን ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ሁለቱን መሪዎች ትናንት ያገናኟቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ናቸው፡፡
5. በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ አንድ ሕጻን እና አንድ ታዳጊን በተለያዩ ጊዜያት የጠለፈ ግለሰብ የ25 ዐመት እስር እንደተፈረደበት ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ ተከሳሹ ለእያንዳንዳቸው 30 እና 70 ሺህ ብር ጠይቆ፣ በድምሩ 35 ሺህ ብር ተቀብሏል፡፡
6. አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንያ በናይል ወንዝ ላይ ለኡጋንዳ ሃይል ማመንጫ ለመገንባት እንደጠየቀ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ 840 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ግንባታ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ይጠይቃል፡፡ ሃሳቡ ከጸደቀ ማመንጫው የኡጋንዳ ትልቁ ሃይል ማመንጫ ይሆናል፤ የኤሌክትሪክ ሃይል መጠኗንም በ40 በመቶ ያሳድግላታል፡፡
@dimtsiweyane1967
@Dweyane1967bot
BY ኣልፋ ጥዕና
Share with your friend now:
tgoop.com/Dweyane1967/2347