tgoop.com/Dweyane1967/2352
Last Update:
ቤቲንግ እንዲቆም ተወስኗል?
በሴቶች ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክተር አቶ አለሙ ሰኢድ፦
"የስፖርት ውድድር [ቤቲንግ] እንዲቆም ተወስኗል። 26 አባላት ያቀፈ የፌደራል የአሉታዊ መጤ ልማዶችና አደንዛዥ ዕፆች ግብረ ኃይልና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተሳተፊ የሆኑበት መድረክ በማዘጋጀት የስፖርት ውድድር በዜጎች ስነልቦና፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና አጠቃላይ የሚያደርሰውን ችግር ተፈትሿል። በጥር ወር ውስጥ ለስፖርት ውድድር በሚል ይሰጥ የነበረው ፍቃድ የቆመ ሲሆን፤ ስራ ላይ የሚገኙ አቋማሪ ድርጅቶች የውላቸው ጊዜ እስኪጠናቀቅ ብቻ ሊቆዩ ይችላሉ።"
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገ/ሚካኤል ሀጎስ፦
"በህጉ መሰረት እየሰሩ የሚገኙ አወራራጅ ድርጅቶች የውል ጊዜያቸው ሲያበቃ ውላቸውን ማደስ ይችላሉ። አሁን ላይ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፍቃድ ያላቸው 46 አወራራጅ ድርጅቶች አሉ። በአዲስ መልክ ፍቃድ መስጠት አቆምን እንጂ ፍቃድ ያለቸውን ድርጅቶች ስራቸው እንዲያቆሙ አልተወሰነም፡፡ ለአወራራጅ ድርጅቶቹ ፈቃድ የሚሰጠው እና በተቀመጠላቸው የአሰራር ህግ መሰረት መንቀሳቀሳቸውን የሚከታተለው ተቋም ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር እንጂ ሌላ ተቋም የለም። የተለያዩ ተቋማት በስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች ዙሪያ የሚሰጡት አስተያየት ትክክል አይደለም።"
[አዲስ ዘመን ጋዜጣ]
@dimtsiweyane1967
@Dweyane1967bot
BY ኣልፋ ጥዕና
Share with your friend now:
tgoop.com/Dweyane1967/2352