tgoop.com/ETHIO_ARSENAL/262547
Last Update:
▪️|| እዉን አርሰናል ማቲያስ ኩኛ ያስፈልገዋል ?
- የዝዉዉሩ ወሬ በጣም Early stage እንደሆነ አዉቃለሁ ነገር ግን ብዙ ነገር ከ rumour ነዉ የሚጀምረዉ ። ባይሳካ እንኳን አርሰናል ምን አይነት ተጫዋች እንደሚፈልግ ማሳያ ነዉ ። ማቲያስ ኩኛ የመጀመሪያ ቦታዉ በ profile እንደተቀመጠዉ striker ነዉ ። ነገር ግን left winger ፣ ወጣ ያለ ወይም ይሄ Right Far winger የሚባል ተጫዋችም ነዉ ። ምን ማለት ነዉ የተጋጣሚ ሳጥን ዉስጥ ብዙ ደቂቃ የሚያሳልፍ ሳይሆን ከጥልቅ ተነስቶ የሚጫወት የ መስመር ተጫዋች አይነት ነዉ ። በግሌ ያን ያህል ረጅም ዓመት አይቼዉ አውቃለሁ ባልልም በቂ በሚባል ሁኔታ የተወሰኑ ጨዋታ ተመልክቻለሁ ። በ አትሌቲ እያለ ባየሁት በጣት የሚቆጠር ጨዋታ ከ መስመር ይልቅ የፊት አጥቂ ይመስል ነበር ። more 4-4-2 እንደ ሁለተኛ አጥቂ አይነት ነገር ። እንግሊዝ ከመጣ በኋላ ግን አጥቂ ቦታ የሚሰለፍ ግን ከጥልቅ በመስመር መጫወት የሚያበዛ አይነት ተጫዋች ነዉ ።
- I don't know ግን በሲቲ ቤት ጄሱስ በጣም ምርጥ በነበረበት ሰአት ጋር ትንሽ የመመሳሰል ባህሪ ነዉ ። ሁለቱም ታጋይ ናቸዉ ፣ ከ poacher ይልቅ false 9 ይመስላሉ ። technical ናቸዉ ፣ ድሪብል ያደርጋሉ ። ስለ አሁኑ ጄሱስ ሳይሆን ሲቲ ቤት ከ ጉልበት ጉዳቱ በፊት ስለነበረዉ ጄሱስ ነዉ የምለዉ ። መሉ በሙሉ ባልልም DNAያቸዉ የተወሰነ ይመሳሰላል ። ግን more ኩኛ direct ነዉ ፣ breakthrough ያደርጋል ፣ ለማግባት ወደፊት የሚሄድ አይነት ተጫዋች ነዉ ። አርሰናል አሁን ማቲያስ ኩኛ ወይስ ሌላ ተጫዋች ያስፈልገዋል ለመመለስ ገና ነዉ ። እንደ መስመር አጥቂ ካሰቡት ምን ማለት ላይሆን ይችላል ። ግን ስጋቴ ኩኛን እንደ ፊት አጥቂ አስበዉ ካመጡት ግን መገለፅ ይኖርበታል ። እንደዛ እንደማይሆን አስባለዉ ።
• ግን በግሌ አርሰናል የሚያስፈልገዉ የ ፊት መስመር ተጫዋቾች type ብዬ የማስበዉ..ተጫዋቾቹ ሳይሆን እንደ እነሱ የሚጫወት ተጫዋች ማለቴ ነዉ !
- የ መስመር አጥቂ : ሊያዎ ፣ ባርኮላ ፣ ዊሊያምስ ፣ ማርሙሽ ፣ ክቫራስኬሊያ አይነት አንድ ለ አንድ ገዳይ የሆኑ ተጫዋቾች !
- የፊት አጥቂ : አይዛክ ፣ ዮኬሬሽ ፣ ቭላሆቪች አይነት ሳጥን ዉስጥ ጨካኝ አጥቂዎች አይነት ይፈልጋል ።
* ከእነዚህ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ተጫዋች ያስፈልገናል ። በጥር ግን እንደዚህ አይነት ዝዉዉር ህልም ነዉ ። ታዲያ አሁን የሳካን ቦታ ለመሸፈን ከዛ ደግሞ እንደሚሰጠዉ ሚና ለመጫወት ማቲያስ ኩኛ ያስፈልገናል ብላችሁ ታስባላችሁ ሀሳባችሁን አጋሩኝ ።
"SHARE" . @ETHIO_ARSENAL
BY ETHIO ARSENAL
Share with your friend now:
tgoop.com/ETHIO_ARSENAL/262547