Telegram Web
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት  "    ]
             
             [     ክፍል ስድስት    ]

❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                         👇
🔥1
                       †                        

† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †

🕊

† በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ ዓበይት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::

    🕊  †  የጠበል በዓል  †   🕊

† ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች::

🕊                      💖                    🕊

❝ ድንግል ያንቺ ልቅሶ በእጅጉ ይበቃኛል ፡ ሁለተኛ እንዳላለቅስ በታምርሽ አድኚኝ ፥ አንች ሁልጊዜም የአዳምና የልጆቹ መድኃኒት ነሽና ኃጥአንን በቸርነቱ እስከአዳነ ድረስ ንጉሥ ልጅሽ ራቁቱን እንደተሰቀለ አስቢ፡፡ ❞
                
[ አባ ጽጌ ድንግል ]


† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
5
3
🕊

[ † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ ዓበይት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::

†  ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ ምድረ ግብጽ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኳን ለስደተኛ በቤቱ ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት ያውቀዋል::

† ለዛም ነው ሊቁ በቅዳሴው :-

"አዘክሪ ድንግል ረሃበ ወጽምዐ : ምንዳቤ ወኀዘነ : ወኩሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ" ያለው::

ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት ድንግል እመቤታችን ውኃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች : ግን ጥርኝ እንኳ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች:: ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች ወስደውት ደረሰች::

ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውኃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች::
"በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ::
እምሰብአ ሃገር አልቦ ዘየአምራ ለጽድቅ::
ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀሐቡኒ በሕቅ::
ወአሕጎልኩ ለወልድየ አሳእኖ ዘወርቅ::" እንዳለ ደራሲ::

ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው ሕይወትነት ያለው ማይ [ጠበል] ፈለቀ:: ጌታችን : እመቤታችን: ዮሴፍና ሰሎሜ ከውኃው ጠጥተዋል::

ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ [መድኃኒት] : ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል::
"ከመ ኢይስተይዋ ሰብአ ሐገር ለይእቲ ማይ አምረራ::
ወለርኁቃንሰ ፈውሰ ወጥዕምተ ገብራ::" እንዳለ መጽሐፍ:: [ሰቆቃወ ድንግል]

ከመቶዎች ዓመታት በኋላም ጌታ ጠበል ያፈለቀበት : ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል:: ጠበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል::

† 🕊 የጠበል በዓል 🕊  †

† ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች::

እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት [እምነት] : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ [በመታሸት] : በቅዱሳን አካል [በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .] ይፈውሳል::

እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል [ይፈውሳል]:: [፪ነገ.፭፥፲ (5:10) , ሐዋ.፫፥፮ (3:6) , ፭፥፲፭ (5:15) , ፲፱፥፲፩ (19:11)]

† ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: [ዮሐ.፭፥፩ (5:1) , ፱፥፯ (9:7) ]

† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::

🕊

[ † ሰኔ ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት
፪. የቅዱስ ውኃ (ጠበል) መታሠቢያ
፫. ቅድስት ትምዳ እናታችን
፬. ቅዱስ አውሎጊስ
፭. አባ አትካሮን

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [ አርባዕቱ እንስሳ ]
፫. አባ ብሶይ [ ቢሾይ ]
፬. አቡነ ኪሮስ
፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት]

" ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ:: ግርማው በእሥራኤል ላይ: ኃይሉም በደመናት ላይ ነው:: እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው:: የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን: ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል:: እግዚአብሔርም ይመስገን:: " † [መዝ. ፷፯፥፴፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
#እግዚአብሔር_ሰው_ይፈልጋል!"

#ልቡ_ንጹሕ የኾነውን፣ አሳቡ የተቃናውን፣ ማግኘት የማይለውጠውን፣ #ይቅርታ አድራጊውን፣ ለእውነት ተቆርቋሪውን፣ ተለሳልሶ የማይናደፈውን፣ #ለፍቅር ዋጋ የሚከፍለውን፣ አድሮ የማይቀለውን፣ በየወንዙ አቋሙን የማይለውጠውን፣ ለጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደውን፣ ለቆዳው ሳይኾን ለቅንነቱ የሚጨነቀውን፣ #የሃይማኖት_አባቶችን የሚያከብረውን፣ ለመታዘዝ ራሱን ያዘጋጀውን፣ ክስና ክርክርን የናቀውን፣

#ልጄ_ኹይ_ሰው_ኹን ፩ነገ ፪፥፪

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
8
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ክብርት ሰንበት   ]        🕊


❝ አሁን ማንኛውም ቁርባኑ [ ሥጋውና ደሙ ] በተሠራበት ቤተ ክርስቲያኑ ጌታችን ስለማይለይ ፣ ሰንበትን እያከበርን መሆናችንን መናገር እንችላለን።

ይህች ሰንበት [ ቁርባን የተሠራባት ማንኛውም ዕለት ] እያከበርናት ያለነው ለምትመጣው ሰንበት ምሳሌ አድርገን አይደለም ፤ በመንግሥቱ ውስጥ ሆነን ሰንበታችንን [ ዕረፍታችን ክርስቶስን ] ፊት ለፊት የምናይባትን የምትመጣዋ ሰንበት መያዣ አድርገን እንጂ። ❞

[  ሊቅ ቀሲስ ታድሮስ  ]

🕊

❝ በነቢዩ በዳዊት መዝሙር በታወቀች በበዐላችን ቀን በእውነት ሃሌ ሉያ እንበል ፣ [ ይህች ቀን ያልታወቀች ያይደለች ] እግዚአብሔር ሥራውን ይሠራ ዘንድ የጀመረባት በእውነት የታወቀች ናት።

ወዮ ይህቺ ዕለት ቀዳሚት ናት ደኃራዊት አይደለችም ፣ ወዮ ይህቺ ዕለት ለዘላለሙ የምትሠለጥን [ ሰፋኒት ወይም ለዘላለም ጸንታ የምትኖር ] ደኃራዊት ናት ፤ ወዮ ይህቺ ዕለት ለአብርሃም ተገለጸች ፣ እርሱንም አስመኘች ፣ ትንቢትም አናገረች እርሱንም ደስ አሰኘች። ❞

†    🕊   ክብርት ሰንበት   🕊    †


🕊                       💖                     🕊
👏1
                       †                        

  🕊    †   የጠበል በዓል   †     🕊

💖                    🕊                     💖

† ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች::

እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት [እምነት] : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ [በመታሸት] : በቅዱሳን አካል [በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .] ይፈውሳል::

እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል [ይፈውሳል]:: [፪ነገ.፭፥፲ (5:10) , ሐዋ.፫፥፮ (3:6) , ፭፥፲፭ (5:15) , ፲፱፥፲፩ (19:11)]

† ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: [ዮሐ.፭፥፩ (5:1) , ፱፥፯ (9:7) ]

† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                       †                        

🕊

† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::

    🕊  †  የጠበል በዓል  †   🕊

[ ለእህታችን የተፈጸመ ድንቅ ተአምር ]

በአንጀት ካንሰር በሽታ በጽኑ ታማ ለስምንት ዓመታት በጽናት እግዚአብሔርን ስትማጸን ቆይታ በሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ጸበል የተፈወሰችና ተአምር የተፈጸመላት እህታችን ታሪክ

[ ክፍል - ፩ - ]

† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
2025/07/12 15:56:55
Back to Top
HTML Embed Code: