This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 [ ዓ ይ ኖ ቼ ና ል ቤ ም ] 🕊
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ እግዚአብሔርም አለው። በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ ፤ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ። ❞ [ ፩ነገሥ.፱፥፫ ]
❝ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ፥ ❞ [ ማቴ.፳፩፥፲፫ ]
🕊 💖 🕊

❤4
🕊
[ † እንኳን ለጻድቅና ሰማዕት አባ ቴዎድሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † አባ ቴዎድሮስ † 🕊
† አባ ቴዎድሮስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ግብፃዊ አባት ነው:: ተወልዶ ባደገባት የእስክንድርያ ከተማ ብሉያትንና ሐዲሳት በወቅቱ ከነበሩ አበው ሊቃውንት ተምሯል:: ጊዜው ምንም መናፍቃን የበዙበት ቢሆን በዛው ልክ እነ ቅዱስ እለ እስክንድሮስና ቅዱስ አትናቴዎስን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና ከነሱ የሚገባውን ወስዷል::
አባ ቴዎድሮስ "አባ" ያሰኘው ሥራው:- ሲጀመር ገና በወጣትነቱ ድንግልናንና ምንኩስናን በመምረጡ ነበር:: ምንም እንኳ ሐብት ከእውቀት ጋር ቢስማማለትም ይሕ እርሱን ከምናኔ ሊያስቀረው አልቻለም:: ከከተማ ወጥቶ: በዓት ወስኖ በጾምና በጸሎት ተወሰነ::
በ፫፻፵ [340] ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ግን በምዕመናን ላይ ከባድ ችግር ደረሰ:: የወቅቱ ነገሥታት በስመ ክርስቲያን አርዮሳውያን ነበሩና ሕዝቡን ማስገደድ: አንዳንዴም የአርዮስን እምነት ያልተቀበለውን ማስገደል ጀመሩ:: በዚህ ምክንያትም ታላቁ የኦርቶዶክስ ጠበቃ ቅዱስ አትናቴዎስን ከመንበሩ አሳደዱት:: በምትኩም አርዮሳዊ ሰው ዻዻስ ተብሎ ተሾመ:: ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ እውነተኛ እረኛ ያስፈለገው::
በበዓቱ የነበረው አባ ቴዎድሮስ አላቅማማም:: ቤተ ክርስቲያን ትፈልገዋለችና መጻሕፍትን ገልጾ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ምዕመናንን ያጸናቸው ጀመር:: መናፍቃኑን ተከራክሮ ምላሽ በማሳጣት ሕዝቡን ከኑፋቄ በመጠበቅ የሠራው ሥራ ሐዋርያዊ ቢያሰኘውም ለአርዮሳዊው ዻዻስ [ጊዮርጊስ ይባላል] ሊዋጥለት አልቻለም:: በቁጣ ወታደሮችን ልኮ አባ ቴዎድሮስን ተቆጣው:: እንዳያስተምርም ገሰጸው:: አባ ቴዎድሮስ ግን እሺ ባለማለቱ ግርፋት ታዘዘበት::
ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲገርፉት ረድኤተ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከዛ ሁሉ ግርፋት አንዲቷም አካሉ ላይ አላረፈችም:: በዚህ የተበሳጨው አርዮሳዊ ዻዻስ የአባ ቴዎድሮስን እጅና እግር ከፈረስ ጋሪ በኋላ አስረው በኮረኮንች መንገድ ላይ በፍጥነት እንዲያሮጧቸው አዘዘ::
ፈረሶቹ መሮጥ ሲጀምሩ የአባ ቴዎድሮስ አካሉ ይላላጥ ጀመር:: ትንሽ ቆይቶ ግን እጆቹ ተቆረጡ:: በኋላም ራሱ ከአንገቱ ተለይታ መንገድ ላይ ወደቀች:: አካሉ በሙሉ መሬት ላይ ተበታተነ:: እግዚአብሔር ቅድስት ነፍሱን ተቀብሎ አሳረጋት::
† ለቅዱሱም ፫ [ 3 ] አክሊል ከሰማይ ወርዶለታል :-
፩. ስለ ፍጹም ምናኔውና ድንግልናው
፪. ስለ ሐዋርያዊ የወንጌል አገልግሎቱ
፫. ስለ ሃይማኖቱ ደሙን አፍስሷልና
"እምአባልከ ተመቲራ ለእንተ ሠረረት ርዕስ:
እግዚአብሔር አስተቄጸላ በአክሊል ሠላስ" እንዳለ መጽሐፍ::
ምዕመናን ሥጋውን ሰብስበው በዝማሬና በማኅሌት በክብር ቀብረውታል::
† አምላካችን ከቅዱሱ በረከት ይክፈለን::
🕊
[ † ሰኔ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ቴዎድሮስ ሰማዕት
፪. አባ ገብረ ክርስቶስ
፫. ፵ "40" ሰማዕታት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅድስት ደብረ ቁስቋም
፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፯. ቅድስት ሰሎሜ
፰. አባ አርከ ሥሉስ
፱. አባ ጽጌ ድንግል
፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል
† " መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይህንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያሰረክባል:: ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም:: " † [፪ጢሞ.፬፥፯] (4:7)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤1👏1
#የክርስቶስ ደም ስላናንተ እንደፈሰሰ አስታውሱ, ያኔ የሕይወታችሁን ዋጋ በሚገባ ታውቁታላችሁ እናም በዓይናቹ ፊት ውድ ይሆናል እናም በከንቱ ሕይወት አታባክኑትም, ምክንያቱም በዋጋ ተገዝታቹሃልና.
አቡነ ሺኖዳ ✍️
“ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam

❤9🙏1
🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ጥበብ ለራሷ ቤት ሠራች ! ]
🕊 💖 🕊
❝ አብ በአካሉ ፍጹም አንድ ነው ፤ ወልድም በአካሉ ፍጹም አንድ ነው ፤ መንፈስ ቅዱስም በአካሉ ፍጹም አንድ ነው። እሊህ ሦስቱ እንደ መንግሥት መዐርግ አይደሉም። ባሕርያቸው አንድ ፣ አገዛዛቸው አንድ ፤ አምላክነታቸውም አንድ ነው እንጂ ፤ ሰማይን ምድርን ፤ ባሕርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር አንድ ነው። [ ዘፍ.፩፥፳ ። መዝ.፶[፵፱]፥፮ ፣ ሮሜ.፩፥፳ ]
በኋላ ዘመንም ገብርኤል መልአክ ወደ ንጽሕት ድንግል ማርያም በተላከ ጊዜ ጸጋ ክብርን የተመላሽ ድንግል እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋን ከነፍስሽ ነፍስን ነሥቶ ሰው ይሆናልና ፤ ክብር ላንቺ ይገባል ብሎ በነገራት ጊዜ ያንጊዜ ሳይወሰን በማይመረመር ግብር ያለዘርዐ ብእሲ በመስማት ብቻ ቃል በማሕፀኗ አደረ። [ሉቃ.፩፥፳፮—፴፱]
ጥበብ ለራሷ ቤት ሠራች ፤ በሰባት አዕማድም አጸናችው ተብሎ እንደ ተጻፈ ፤ ጥበብም የተባለ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ እግዚአብሔር ቃል ነው ፤ የሠራችው ቤት የተባለም ከድንግል ፈጥሮ የተዋሐደው ሥጋው ነው ፤ ይህም በነፍስ በሥጋ ፍጹም የሚሆን ትስብእቱ ነው። ሰባቱ አዕማድም ሰባቱ የሐዲስ ሕግ መጻሕፍት ናቸው ፤ ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ክርስቶስ አምላክ ፤ ሰው በመባል ሳይለይ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ። [ምሳ.፱፥፩ ። ማቴ.፲፩፥፳ ። ኤፌ.፫፥፲-፲፪ ] ❞
[ 🕊 ቅዱስ ቄርሎስ 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ ዛ ሬ ም ሽ ት ! ]
♱ ♱ ♱ ♱ ♱ ♱ ♱
❝ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው ፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ❞ [ ማቴ.፭፥፲ ]
🕊 💖 🕊
- ስለ ሃይማኖታቸው ብለው ከሃገር ለተሰደዱት ወንድሞቻችን እፎይና ጰላድዮስ ድጋፍ
- በወንድማችን እፎይ የቲክ ቶክ ገጽ ላይ ልዩ መርሐ-ግብር ተዘጋጅቷል
- ዛሬ ምሽት 01:00 ላይ መላው ኦርቶዶክሳዊ እንዲገኝ ተጋብዟል።

❤3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
🕊 [ መ ካ ከ ለ ኛ ! ] 🕊
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ አንድ እግዚአብሔር አለና ፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ❞ [ ፩ጢሞ.፪፥፭ ]

❤2
🕊
[ † እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ † 🕊
† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው : በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው::
ሊቁ የተወለደው መጋቢት ፳፯ [27] ቀን በ፬፻፴፫ [433] ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር::
አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት : ገና በ ፫ [3] ዓመቱ : እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ ፫ [3] ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ::
† ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም :-
፩. ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ::
፪. ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ::
፫. ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው::
ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል::
ቅዱስ ያዕቆብ ፯ [7] ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ፭ [5] ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ፲፪ [12] ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን:: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው::
"እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል::
ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን : ዕጸበ ገዳምን : ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ [በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት] ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
† በዘመኑም :-
፩. የ፬፻፶፩ [451] ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል::
፪. ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል::
፫. በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል::
4፬. ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::
በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ፸፪ [72] ዓመቱ በ፭፻፭ [505] ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ ፳፯ [27] ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች::
† አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን::
🕊
[ † ሰኔ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ
፪. ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን [ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው]
፫. ፲፮ ሺህ "16,000" ሰማዕታት [በአንድ ቀን የተገደሉ]
፬. የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር [CAIRO] ውስጥ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ሥሉስ ቅዱስ [ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ]
፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫. አባ ሲኖዳ [ የባሕታውያን አለቃ ]
፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭. አባ ባውላ ገዳማዊ
፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯. ቅዱስ አግናጥዮስ [ ለአንበሳ የተሰጠ ]
† " ይሕንን እዘዝና አስተምር :: በቃልና በኑሮ : በፍቅርም : በእምነትም : በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው:: እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር : ለማስተማርም ተጠንቀቅ:: " † [፩ጢሞ.፬፥፲፩] (4:11)

🥰1
በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ የልብኽንም መሻት፡ይሰጥሃል መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ በርሱም ታመን ርሱም ያደርግልኻል ፤ ጽድቅህን እንደ ብርሃን ፍርድህንም እንደ ቀትር፡ያመጣል።
ለእግዚአብሔር ተገዛ ተስፋም አድርገው መንገድም በቀናችለትና ጥፋትን በሚያደርግ ሰው አትቅና ከቍጣ ራቅ መዓትንም ተው እንዳትበድል፡አትቅና ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ፡ምድርን፡ይወርሳሉ።
መ.ዝ 37 ÷ 4-9

❤13