Telegram Web
7
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው። ❞  [ መዝ . ፻፲፱ ፥ ፱  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]

          [   ክፍል -  አሥራ ሦስት  -    ]

            💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ለዝሙት የሚያነሳሱ ቦታና ጊዜያት !  ]


የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]


🕊                        💖                      🕊
                             👇
4
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🕊                       ❤️‍🩹                      🕊

[       የካቲት ፳፫ / 23 አድዋ      ]

🕊 እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ 🕊

🕊                       ❤️‍🩹                      🕊

እነርሱ ... በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ❞ [ ዕብ.፲፩፥፴፫ ]

▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

❝ የካቲት ፳፫ ፲፰፻፹፰ ዓ.ም [march 1 1896] አነጋጉ ላይ በቤተክርስቲያኑ የነበረው ሁሉም ሰዉ ቅዱስ ቁርባንን ተቀበለ፡፡ ከዚያም አረንጓዴ ፣ ቢጫና ቀይ ቀለም ያለው ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ቅርፅ ተሰቀለ፡፡ የቆረብነውም ሁሉ ጎንበስ ብለን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገሪቱን ፤ ንጉሰ ነገሥቱን እና ኃይማኖቱን እንዲያስጠብቅና እንዲረዳን ለመንን፡፡ እንደ ነጋም ጦሩ ሁሉ የጦር መሳሪያውን ታጥቆ ወደ ውጊያ ገባ።❞

[ ከዳግማዊ ምኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ መፅሐፍ የተወሰደ ]

🕊                       ❤️‍🩹                      🕊

❝ እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ ፥ ጽድቅን አደረጉ ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ ፥ ከድካማቸው በረቱ ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ❞ [ ዕብ.፲፩፥፴፫ ]

- " አድዋ ባ'ፍ አይገባም "
- [ በገጣሚ አበባው መላኩ ]

         †               †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👏4
                     †                       

[       የካቲት ፳፫ / 23 አድዋ      ]

🕊 እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ 🕊

💖

የልዳ ሰማዕት የፋርሱ ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት [ አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት ] ቀን።

የካቲት ፳፫/23 አድዋ !


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
5
እንኳን ለኢትዮጵያ ገበዝ (ጠባቂ) ለአድዋው አርበኛ፣ ለፍጡነ ረድኤት፣ ለገባሬ ተአምር ሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ በ1888ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ንጉሠ ነገሥትን ምኒልክና ሰራዊቱ ለረዳበት፤ ኢትዮጵያ በሮማውያንን (ጣልያንን) ድል ለተቀዳጀችበት ለ129 (ለአንድ መቶ ሃያ ዘጠነኛ) ለአድዋ በዓል በሰላም አደረሰን

ለመቀላቀል👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
17
🕊

[  † እንኳን ለታላቁ ሐዋርያና ሰማዕት ቅዱስ ፖሊካርፐስ እና ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †   ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊    ቅዱስ ፖሊካርፐስ    🕊

† ቅዱስ ፖሊካርፐስ :-

+ ከ፸ [70] እስከ ፻፶፮ [156] ዓ/ም የነበረ::
+ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ከመሰከረላቸው ፯ [7]ቱ አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ [የሰርምኔስ] ዻዻስ የነበረ::
+ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቃል በቃል የተማረና ደቀ መዝሙሩ የነበረ አባት ነው::

ታላቁ አግናጥዮስ [ምጥው ለአንበሳ] የዚህ ቅዱስ ባልንጀራ ነበር:: ከ፵፮ [46] ዓመታት በላይ በፍፁም ትጋት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎ አረማውያን በ፹፮ [86] ዓመቱ በአደባባይ በእሳት አቃጥለው ገድለውታል:: አባቶቻችን "ሐዋርያዊ" ሲሉ ይጠሩታል::


🕊  †  ዳግመኛ በዚህ ዕለት በ፩፰፻፹፰ [1888] ዓ/ም በቅዱስ ጊዮርጊስ ምልጃና ረዳትነት አባቶቻችን አድዋ ላይ ጣልያንን ድል አድርገዋል:: ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ደጉን ንጉሥ ዳግማዊ አፄ ምኒልክን እናስባቸው ዘንድ ይገባል::


🕊  † ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት †  🕊

በቤተ ክርስቲያን ስመ ጥር ከሆነ ቅዱሳን ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ አውሳብዮስ ነው:: ተወልዶ ያደገው በምድረ አንጾኪያ (ሶርያ) ሲሆን ዘመኑም ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፋሲለደስ ነው:: እናቱም ቡርክት ሶፍያ ትባላለች::

ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ ትንሽ ወንድሙ መሆኑም ይታወቃል:: ቅዱሳን እነ ፊቅጦር : ገላውዴዎስ : ቴዎድሮስ : ዮስጦስ : አባዲር . . . ባልንጀሮቹ ሆነው ኑረዋል::

ቅዱስ አውሳብዮስ የቅዱስ ፋሲለደስ ፍሬ ነውና ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር ሆነ:: በቤተ መንግስት ውስጥ ስንት የተደላደለና የተቀማጠለ ነገር እያለ እርሱ ግን እንደ ቡሩክ አባቱ ንጽሕናን መረጠ:: የወርቅ ካባ ደርቦ ሲሰግዱ ማደር ምን ይደንቅ!

ያ ዘመን እጅግ ግሩም የሆኑ ቅዱሳን በቤተ መንግስት የታዩበት ነበር:: ቅዱስ አውሳብዮስ በምጽዋት : በጾምና ጸሎት የሚኖር ቢሆንም በየጊዜው ወደ ጦርነት ይላክ ነበር:: ምክንያቱም እርሱ ኃያል የጦር ሰው : የሠራዊቱም ሁሉ አለቃ ነውና:: በሔደበት ሁሉም በእግዚአብሔር ኃይል ድል ያደርግ ነበር::

አንድ ጊዜም ከፋርስ ቁዝ ሰዎች ጋር ጦርነት ውስጥ ገቡ:: ይህንን ጦርነት በበላይነት እንዲመሩ ቅዱሳን አውሳብዮስና ዮስጦስ በኑማርያኖስ [ንጉሡ ነው] ተሹመው ወደ ሠልፍ ገቡ::

በጦርነቱ ጐዳና ላይ ሳሉ ግን አንድ አታላይ ሰላይ በጠላት እጅ እንዲወድቁ አደረጋቸው:: የተማረኩና የታሠሩ ዮስጦስና ሠራዊቱ ሲሆኑ ቅዱስ አውሳብዮስ ይህን ሰምቶ አለቀሰ:: ወደ ፈጣሪውም እየተማጸነ ለመነ::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ አረጋጋው:: ድል መንሳትንም ሰጥቶት አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ዮስጦስን አስፈታው:: ጠላቶቻቸውንም እያሳደዱ አዋረዷቸው:: "ወመጠውከኒ ዘባኖሙ ለጸርየ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ::

ከዚህ ሠልፍ በሁዋላ ቅዱሳን አውሳብዮስና ዮስጦስ በድል አድራጊነት ወደ አንጾኪያ ሲመለሱ ግን አንጀትን የሚቆርጥ ዜና ደረሳቸው:: አምላከ አማልክት ክርስቶስ ተክዶ ጣዖታት [እነ አዽሎን : አርዳሚስ] እየተሰገደላቸውም ደረሱ:: ይህንን ያደረገ ደግሞ የሰይጣን ታናሹ የሆነ ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ነው::

ቅዱሳኑንም ለጣዖት ስገዱ ሲል በአደባባይ ጠየቃቸው:: ድፍረቱ ያናደደው ቅዱስ አውሳብዮስ ግን ሰይፉን መዞ ወደ ንጉሡ ተራመደ:: ያን ጊዜ ንጉሡ ሸሽቶ ሲያመልጥ መሣፍንቱን ሜዳ ላይ በተናቸው:: አባቱ ቅዱስ ፋሲለደስ ባይገለግለው ኖሮ ኃያል ነውና ባላተረፋቸው ነበር::

ከቀናት በሁዋላ ግን ቅዱስ አውሳብዮስ በጾምና ጸሎት ሰንብቶ ሰማዕት ለመሆን ልቡ ቆረጠ:: ቅዱስ ሚካኤልና አባቱ ፋሲለደስም በምክር አበረቱት:: እርሱም በአጭር ታጥቆ በከሐዲው ንጉሥ አደባባይ ላይ ቆመ::

"እኔ ክርስቲያን ነኝ:: ክርስቶስን አመልካለሁ:: ለእርሱም እገዛለሁ:: ጣዖታት ግን ድንጋዮቸ ናቸውና አይጠቅሙም:: የሚሰግድላቸውም የረከሠ ነው::" ሲል አሰምቶ ተናገረ:: ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ እዚያው ሊገድለው ፈልጐ ነበር:: ቅዱሱ ተወዳጅ ሰው ነበርና ሁከት እንዳይነሳ አውሳብዮስ ወደ አፍሪቃ [ግብጽ] ሒዶ እንዲገደል ተወሰነበት::

በምድረ ግብጽም አረማውያን በእሳትም : በግርፋትም : በስለትም ብዙ አሰቃዩት:: ቅዱስ ሚካኤል ግን ገነትን አሳይቶ ከደዌው እየፈወሰ ተራዳው:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ገድለውት አክሊለ ክብርን ተቀዳጅቷል::

† አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት ጽናታቸውን አድሎ ከበረከታቸው ይክፈለን::

🕊

[   † የካቲት ፳፫ [23] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ፖሊካርፐስ ሐዋርያዊ ሰማዕት [የሰርምኔስ ዻዻስ]
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት [አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት]
፫. ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት [የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ]
፬. ቅዱስ አውስግንዮስ ሰማዕት

[    † ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪. ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
፫. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፬. አባ ሳሙኤል
፭. አባ ስምዖን
፮. አባ ገብርኤል

" በሰርምኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልዐክ እንዲህ ብለህ ጻፍ:- ሞቶ የነበረው: ሕያውም የሆነው: ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል :- 'መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ . . . እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን: የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ::" † [ራእይ.፪፥፰] (2:8)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
👍2
8
#_አድዋ_

#ውብ_የኢትዮጵያ_እና_የተዋሕዶ_ታሪክን
እጅጉን በአጭሩ እናጫውታችሁ


አንድ የኢጣሊያ እስረኛ ንጉስ አጴ ምኒልክ የተማረኩ እስረኞችን በሚፈቱበት ዕለት #እንዲህ_አላቸዉ ?

ንጉስ ሆይ ያኔ ጦርነት ሲካሄድ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ወታደረዎትን ይመራ የነበረው የኛን ትጥቅ የሚመስል የለበሰው #ጄኔራሎት አንዴ ያሳዩኝ አላቸው

#እርሳቸውም ማን እንደሆነ ገባቸውና "#እሱማ_የኢትዮጵያ_ንጉስ_ነው" ብለው ሲመልሱለት በመደንገጥ "እርስዎስ አላቸው "እርሳቸውም እኔማ #ባሪያው_ነኝ"
አሉት ።
በዚህ የተነሳ በየዓመቱ አራዳ #ጊዮርጊስ እዲነግስ አደረጉ።

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
10👏1
                     †                     

[   የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ]

[       🕊   ቅድስት   🕊      ]

💖

" ቅድስት " ማለት ‹ የተለየች ፣ የነጻች ፣ የከበረች › ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ጾም የጀመረባት ፣ ልዩ ፤ የተቀደሰች ፤ የከበረች ፤ ልዩ ፣ ንጹሕ ፣ ክቡር በሚኾን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጾመች መኾኗን ያመላክታል፡፡

ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት የተገለጠችው የጌታችን ጾም ስትኾን ፣ ስያሜዋና የዕለቷ የምስጋና ሥርዓትም የቅዱስ ያሬድ ነው፡፡አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት እነዚህ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡

ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የሚባሉትም ፦ ትዕቢት ፣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሦስት ኃጢአቶች ጌታችን በዲያሎስ በተፈተነ ጊዜ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና ፤ በስስት ቢመጣበት በትዕግሥት ፤ በፍቅረ ንዋይ ቢመጣባት በጸሊዓ ንዋይ ጌታችን ዲያሎስን ድል አድርጎታል፡፡ ለእኛም እነዚህን ድል ለማድረግ የምንችልበትን ጥበብ – ጾምን ገልጦልናል፡፡

ትዕቢት ያልተሰጠንን መሻት ፣ ስስት አልጠግብ ባይነት ስግብግብ መኾን ፣ ፍቅረ ንዋይ ለገንዘብ ሲሉ ፈጣሪን መካድ ነው፡፡ አንደ ክርስቲያን ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል ካደረገ ሌሎችን ኃጣውእ በቀላሉ ድል ማድረግ ይቻለዋል፡፡

[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]


🕊       [   ክብርት ሰንበት   ]        🕊

🕊                         💖                     🕊
🙏1
1
🕊                       💖                      🕊

[        የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት       ]

💖

[        🕊     ቅድስት      🕊       ]

ቅድስት ማለት የከበረች የተለየችና የተመሰገነች ማለት ነው ፤ ይኸውም በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው ጌታ ጾምን ቀድሶ የጀመረባት ዕለት በመሆኑ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህ ሳምንት ቅድስት የሚል ሥያሜ ሰጥቶታል::

ይህ ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና እንዲሁም ቅዱስ እግዚአብሔር ስለቀደሳቸው ቅዱሳን አካላት [ ጾም ቅድስት ፣ ሰንበት ቅድስት ፣ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወዘተ እያለች ] የምታስተምርበት ሳምንት ነው።

ሰው ሁሉ በቅድስና መንገድ በመመላለስ የክብሩ ባለቤት የመንግሥቱ ወራሽ እንዲሆን እግዚአብሔር " እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ " በማለት ስለማስተማሩ ስፊ ትምህርት ይሰጥበታል።

እግዚአብሔርን ማየትና የእግዚአብሔር የሆነውን ሥርዓት መከተል ስለሚያስችል ዕለት ዕለት መልካም በማድረግ ቤተ መቅደስ ተብሎ የተነገረለትን ሰውነታችንን በንጽሕና በመጠበቅ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሆነን መቅረብ እንደሚገባን ይዘከርበታል።

እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰንና ልጅነትን እንደሰጠን በማመን በተቀደሰ ሁኔታ መኖር ይገባናል።


🕊                        💖                       🕊
1
Audio
👍1
2025/07/14 03:23:06
Back to Top
HTML Embed Code: