ESAT_TV1 Telegram 20828
ኤርትራ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም ሲሉ የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አስታወቁ‼️

“የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አለ” የሚለውና ተደጋጋሚ የሆነ በተወሰኑ አካላት የሚነሳ ውንጀላ ፍፁም ሀሰት እና ግጭት ለመቀስቀስ ምክንያት ለመፍጠር ነው፤ የኤርትራ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ በሉዓላዊ ግዛታቸው ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ ሲሉ አቶ የማነ ገብረመስቀል ገልፀዋል።

ሚኒስተሩ አክለው ከዚህ ቀደም በብዙ አጋጣሚዎች በማያሻማ መልኩ እንደተገለጸው፣ ኤርትራ የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም፤ በመሰረቱም ስምምነቱ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ኤርትራ በህወሓት የፖለቲካ አንጃዎች ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ ሽኩቻ የማባባስ ፍላጎት የላትም ይህም በትግራይ ህዝብ ላይ አላስፈላጊ እና ሊወገድ የማይችል ስቃይ ያስከትላል ሲሉ ተደምጠዋል።

በቀይ ባህር ዙሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ሌት ተቀን የሚያወጡት የማያቋርጥ ግጭት ቀስቃሽ መግለጫዎች ለአላስፈላጊ ውጥረቱ አባባሽ ምክንያት ሆነው ቀጥለዋል ያሉ ሲሆን ይህ ያለምንም ማወላወል በጠንካራ ሁኔታ መወገዝ አለበት ሲሉም የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አቶ የማነ ገብረመስቀል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት አስታውቀዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1

tgoop.com/Esat_tv1/20828
Create:
Last Update:

BY ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

Share with your friend now:
tgoop.com/Esat_tv1/20828

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Content is editable within two days of publishing Select “New Channel” Users are more open to new information on workdays rather than weekends. How to Create a Private or Public Channel on Telegram? Telegram users themselves will be able to flag and report potentially false content.
from us

Telegram ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
FROM American