tgoop.com/Geb19/1803
Last Update:
📃ያለመጠን የሚያስገርም ልደት❗❗
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሕፃን ተወልዶልናል፣ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፣አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ፣ስሙም ድንቅ መካር፣ኃያል አምላክ ፣የዘለዓለም አባት፣የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።ኢሳ ፱፥፮
••●◉ ✞ ◉●••
🗣እናቱን የፈጠረ ልጅ፤
🗣ፈጣሪዋን የወለደች እናት፤
🗣አባቱ የማይቀድመው ልጅ::
••●◉ ✞ ◉●••
🤷መልክን ከደም ግባት ፣ንፅህናን ከቅድስና አስተባብራ የያዘች እናት ማረፊያ አጥታ እንዴት በበረት ወለደች❓
🤷አለቅነት በጫንቃው የሆነ ጌታ አንዴት በበረት ተወለደ❓
••●◉ ✞ ◉●••
🗣አንደበቶች ሁሉ ስለ እርሱ በጐነት የሚያወሩለት ጉልበቶችም ሁሉ የሚንበረከኩለት የሁሉም ጌታ የሁሉም ሀኪም የሁሉም መድሐኒት የሆነው ጌታ የዛሬ 2014 በከብቶች በረት ከንፅህት ድንግል ተወለደልን❗️ይህ የፍቅሩ ጅማሬ ነው።ተወለደ ስንል ተወለድን ማለታችን ነው❗️
••●◉ ✞ ◉●••
💁♂በበረት የወደቁ ፣ጊዜ የከዳቸው፣የታሰሩ፣የተፈናቀሉ፣የተሰሳደዱ፣በመንገድና በቤት በችግር ያሉ አሉና እናስባቸው።
••●◉ ✞ ◉●••
🧑💻በዚህ ሰጪ ይፀድቅበታል፣ተቀባይ ያመሰግንበታል ሰጥተን ለመፅደቅ፣ተቀብለን ለማመስገን ያብቃን ።
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ተወዳጆች ሆይ ፍቅር ተወልዶልናል
እንኳን አደረሳችሁ ❗️
✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨✝️✨
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን 🙏
💒💒💒💒💒💒⛪⛪⛪⛪⛪⛪
💒 @efr21 📖 @Geb19 ⛪
💒 @Geb19bot 🔊 @Geb19 ⛪
💒 @efr21 🔔 @Geb19 ⛪
💒💒💒💒💒💒💒⛪⛪⛪⛪⛪
BY የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
Share with your friend now:
tgoop.com/Geb19/1803