tgoop.com/Geb19/1811
Last Update:
💁♂አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ ❓" አሉት።
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን።ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን ሰው ሁን ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው።ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።
••●◉ ✞ ◉●••
📜ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው። "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል❓
••●◉ ✞ ◉●••
🙏የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት ይባላል❓ ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን❓
••●◉ ✞ ◉●••
👌በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን❓ በፍጹም አይሆንም❗ የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን❓ እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ❓
••●◉ ✞ ◉●••
💁♂አባ ጊዮርጊስ ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣ ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ ❓ ይል የለምን❓ ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪⛪⛪⛪⛪⛪
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27 ⛪
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪
💒💒💒💒💒💒💒⛪⛪⛪⛪⛪
BY የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
Share with your friend now:
tgoop.com/Geb19/1811