tgoop.com/Geb19/1887
Last Update:
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✍️አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
💁ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም፣ እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤ ታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕዐ ሕይወት ሥር ተቀምጦአየው። የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እን ዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕዐ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ። የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመለሱ።የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግልማርያም አማላጅነት ያማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ፡ ማትያስ ፡ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
💝በዚችም ዕለት ዳግመኛ የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው።የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗልና ስለዚህም እርሷን መው ደዱን የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑየድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በኃያሉ ተጋዳይ በጊዮርጊስም ጸሎት በእኛ ላይ ምሕረት ይቅርታ ቸርነት ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
💁♂️በዚችም ቀን የሶርያ መስፍን ጊጋር በሰማዕትነት ሞተ።ሰማዕት የሆነበትም ምክንያት ጌታችን ከእመቤታችን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ በተሰደደ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ሳለ ኀሮድስ ሰምቶ ከበው ይዘው ይገድሏቸው ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ ጊጋርም ጭፍሮች እንዲያገኙአቸው አሸሻቸው።ስለዚህም ኄሮድስ ተቆጣ ጊጋርንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ሕዋሳቱንም ሁሉ ቆራረጠ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት መታሰቢይውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በሦስት አክሊሎችም ተጋረደ ሦስት አክሊላትን ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
🍀🍀🍀🍀🙏🙏🙏🙏🍀🍀🍀🍀══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
BY የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
Share with your friend now:
tgoop.com/Geb19/1887