tgoop.com/Geb19/1889
Last Update:
🗣ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል‼️🗣
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም::ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ::ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁♂️ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁♂️ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ (ኢሳ 38:5)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው❓ ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው❓በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው❓ ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን❓ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን❓ ይላል መሐሪው (ሕዝ 18፥23)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን❓
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል:: እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን🙏🙏 ══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
BY የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
Share with your friend now:
tgoop.com/Geb19/1889