tgoop.com/Geb19/1902
Last Update:
✍️ደብረታቦር
══════◄✣••✥••✣►══════
ደብረታቦር ማለት በወይራ የተከበበ ተራራ ማለት ። ደብረታቦር ከጌታ ከዘጠኙ በዓላት አንዱ ነው። ወእምድኅረ ስሱ መዋዕል ነሥኦሙ እግዚእ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ወለ ያዕቆብ ወለዮሐንስ እኍሁ ወአዕረጎሙ ደብረ ነዋኃ እንተ ባሕቲቶሙ ማቴ 17:-1 ከስድስተኛው ቀን በኃላ ወደ ጴጥሮስ፣ዮሐንስ፣ያዕቆብን ወደ ተራራ አወጣቸው ማለት በፍልጵስዩስ ከተማ የሰውን ልጅ ሰው ማን ይልዋል ብሎ ጠይቋቸው ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉዉ ኤልያስ ነው የሚሉህ አሉዉ እናተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ የእግዚአብሔር አብ የባህይሪ ልጅ ነህ ቢለው በአንተ ቃል መሰረትነት ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን አንፃታለው።የሲኦል ደጆችም አይበረታቱባትም። ══════◄✣••✥••✣►══════
ነሐሴ 13 ከነቢያት መሴና ኤልያስን። ከሐዋርያት ያዕቆብ፣ጴጥሮስና ዮሐንስን ይዞዎ ካወጣቸው በኋላ ባህርየ መለኮቱን ቢገልጥባቸው ያዕቆብና ጴጥሮስ ወደቁዉ ሙሴም መቃብሬ ይሻለኛል አለ። ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ተነጠቀ። ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ሲሆን ቢወድቁም አትፍሩ እኔ ነኝ አላቸው። ለምን ምስጥሩን በከተማ አላደረገውም ቢሉ በከተማ አድርጎት ቢሆን ምስጢር አፈሳ በሆነ ነበርና። ለምን በታቦር አደረገው ቢሉ ሐዋርያት በሲኖዶስ ታቦር ብለው አንስተውታል። ══════◄✣••✥••✣►══════
ትንቢት ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ ተብሎ ተነግሯል። ምሳሌም ባርቅ ሲሳራን ድል ነሥቶበታል። ጌታም በልበ ሐዋርያት ያደረውን ሰይጣን ድል ነስቶበታል። ከደናግል ኤልያስን ከመአስባን ሙሴ ማምጣቱ መንግሥተ ሰማያትን ማአስባንም ደናግልም እዲወርሳት ሲያጠይቅ ነው ። መልካም በዓል። ══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @eotc27 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
BY የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
Share with your friend now:
tgoop.com/Geb19/1902