tgoop.com/Habibacalligraphy/1909
Last Update:
ክፍል:-18
👣ያልወለደች 🕊 እናት👣
.
.
...."ምን መሰለሽ ፈርሁ"ብሎ አሁንም በረዥሙ ተነፈሰ እኔ ፈርቻለው እኔ ወይ ፋይሰል ከዚ ቤት እንዳልተወለድን መጀመራያም ከ ፋይሰል ጋር ስናወራ ነበር ግን ማናችን ነን?የሚለው ጥያቄ ለሁለታችንም መልስ አልባ ነው አባባ ስሜቱ ተረብሿል "እእ አባባ በአላህ ተናገር ልቤ በአፌ ልትወጣ ነው"አልኩት አይን አይኑን በስስት እያየው "ፋይሰል ወንድምሽ አይደለም"አፈረጠውውው "ምን" ብዬ ከተቀመጥኩበት ተነሳው ፋይሰል ወደ ሳሎን ሊገባ ከበሩ ላይ ነበር እዛው ቆሞ ቀረ ሁሉም ወደበሩ አየ ነቢልና የሀናን ባል ተነሱና ፋይሰልን ወደ ሳሎን አስገብተው ሁሉንም ነገር አረዱት ፋይሰል የዚች ሴትዮ ልጅ ነው! የዛሬ 25 አመት በፉት አንድ የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ ወልዳ እዛው ጥላው የጠፋችው ሴትየዋ መናገር ጀመረች "በሰአቱ ቤተሰቤ ያመጣልኝን ትዳር እንቢ ብዬ የማምነውን ሰው አገባው ነገር ግን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ነበርን ሳንበላ ምንተኛበት ጊዜም ነበር እንደዚ መዛለቅ ስላልቻልን ለትንሽ ጊዜ እኔ ቤተሰቦቼ ጋር ተቀመጥኩኝ ለካ እኔ ሳላውቀሙ የ3 ወር እርጉዝ ነበርኩ ይሆን ባወኩኝ በ ሳምንቱ ለልጄ አባት ነገርኩት ያለንበትን ሁኔታ ስለሚያቅ ቤተሰቧቼ ጋር እንድቀመጥ እሱም ስራ እንደሚፈላልግ ከዛ ስራ ሲያገኝ አንድ ላይ እንደምንኖር ነግሮኝ ተለያየን ከዛ ቀን ብኀላ አይቼው አላቅም ቤተሰቧቼም ለኔ ያላቸው ስሜት ተቀየረብኝ የትውልድ ሀገሬን ጥዬ ወደ አዲስ አባባ ሁሉንም ትቼ መጣው አዲስ አበባ ስመጣ 8 ወር እርጉዝ ነበርኩን መሄጃ ስለሌለኝ የድሮ ሰፈራቹ መግቢያ ጋር ሸራ ወጥረው ኑሮዎን ወደምገፋ ጓየኛዬ ተጠግቼ አንድ ወር ከነሱ ጋር አሳለፍኩኝ ብዙ ጊዜ እንደውም ጋሽ አህመድን ስናያቸው ደስ ይለን ነበር ምንም የዛኔ ዝቅተኛ ኑሮ ላይ ቢሆኑም ያላቸውን ሳይሰጡን ግን አያልፉም ነበር እንደ ድንገት ምጥ ሲጀምረኝ ተሯሩጠው ወደ መንግስት ሆስፒታል ወሰዱኝ ልጄ የኔ እጣ ፈንታ እንዲደርሰው ስላልፈለኩ በወለድኩኝ በ 3ተኛ ቀኑ ጥዬው ጠፋው ምንም ቢገጥመው ከኔጋ የሚያየው ስቃይ አይበልጥም ብዬ ነበር ወዲያው የ ነረብ ሀገር ፕሮሰስ ጨርሼ ወደ ዱባይ ሂድኩኝ እዛም ለ15 አመት ቋየው ከመሄዴ በፊት ወደ ወለድኩበት ሆስፒታል ስለልጄ ላጣራ ሰው ልኬ ነበር የሆነች ሴትዮ ልጅ ወልዳ ስለሞተባት እሷ እንድታሳድገው ቦርዱ ተወያይቶ ለሷ እንደተሰጣት በሰው በሰው አጣራው አጋጣሚው ደስ አለኝ ጋሽ አህመድ ጥሩ ሰው እንደሆኑ አውቃለው ቤታቸውንም ስለማቅ ስለልጄ አጣራ ነበር ብቻ ዱባይ ለ 15 አመት ሰርቼ አሪፍ ህይወት ኞረኝ በዚህ 15 አመት ውስጥ የሰላም እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም ነበርር ከ 20 አመት ብኃላ ወደ ኢትዮጲያ ስመለስ የናንተ አድራሻ ጠፋብኝ ቤትም ቀየራቹ የ ኢትዮጲያ መንገድ ሁሉ ተቀያይሯል እናንተን ለማግኘት አዳጋች ነበር ብቻ አሁን ከብዙ ውጣ ውረድ ብኃላ ተገናኝተናል"አለች እንባ ከ አይኞቿ ቁልቁል ይፈሳል ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ እንደ ድንገት ፋይሰል ብድግ ብሎ ተነሳ ሁሉም አብሮት ቆመ ወደ ሴትየዋ እየተራመደ መናገር ጀመረ"እፈራ የኔ ቤተሰቦች እዚጋር ምታያቸው ሁለቱ ሰዎች ናቸው አምጣ የወለደችኝም እሷ ናት እሷ ሁለተኛ ወደዚ ቤተሰብ እንዳመጪ" ብሎ እጇን እንደ ህፃን ልጅ እየጎተተ ከጊቢ ውጪ አስወጥቶ በሩን ዘጋው ፋይሰል ስሜታዊ ስለነበር ማንም ሊያስቆመው አልታገለም ወደ ሳሎን ገብቶ እየሳቀ "እማማ ቀልድ ነዌ አንቺ ነሻ የኔ እናት 9 ወር አረግዘሽ አምጠሽ የወለድሺኝ አንቺ ነሻ?"የጥያቄ መአት ፋይሲ አስፈርቶኛል እንደ መሳቅ ይላል መልሷ ይኮሳተራል እኔ የሰማሁትን ማመን አቅቶኝ ደንዝዤ ደርቄ ቁጭ ብያለው እማማ እየተንተባተበች "የኔ ልጅ ነህ የ አይኔ አበባ ግን.......
.
.
ክፍል:-➊➒ እና የመጨረሻው ክፍል #ይቀጥላል
JOIN us 👉👉👉
www.tgoop.com/Habibacalligraphy
BY Habiba Calligraphy
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/OnYn4Hrm5pf-MHe85p1XgfjdwHy_QENya-owiYC6408KpjW2IyGACbb7YOgv-O64yk3VscAG6b6wG5qhJAkrUXKLnzwkNz3tXma5zsiH2Hl9Y0GRPx03jO987KNUaZJ7d4I2mEpDBc3zUq8HRnOK2dVxpsRhcj3hm-HpNxXuqLtt3XLfMB1Jw_C1XeXPEfaSj9oiIa7H-8yMhbjiLSvBajPKXP_YWTSBanscMytCyCYOZU04brYeBp3jFU_Y7Q6WBUfBInTT_m90TNSSHRmgrDe5zZRbszx7Pmz6yCistm3FW2ibzY1MRKU_4pbsY-b3ZivAQ6S6dBH5Vwv7nbNJFg.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/Habibacalligraphy/1909