HABIBACALLIGRAPHY Telegram 1934
የባከኑ ቀናት
ክፍል ሁለት
(ሂባ ሁዳ)

አስተማሪው ለምን እንደሆን ባላውቅም <<ለዛሬ ይብቃን>> ብሎ ወጣ።
<<እስይይይ ውልቅ በል ይመችህ>> ባቢ ከዴስኩ ላይ ተቀመጠ። በዚህ ሰዐት ዩስራ እና ራቢያ ወደኔ መጡ።
<<እናንተ የት ጥፍታቹ ነው?>> እንደማኩረፍ ሲያደርገኝ ሁለቱም መጥተው አቀፉኝ። ቀኑን ሙሉ እንዳልተገናኘ ሰው ተቃቀፍን።
<<ኢብቲ ዛሬ የሆነውን ጉድ ብታውቂ! ወደ ቤት ስንሄድ እንነግርሻለን..>> ብላ ለመቀመጥ ስትዞር..
<<እንዴ ባቢቢቢቢ>> ራቢያ ነበረች። ዩስራም ደግመችው፤ከአነጋገራቸው አምናም አንድ ክፍል እንደ ነበሩ ተረዳሁ። እነሱ ሲቀላለዱ ኢክራም መጣች፤ ለካ የምሳ ሰዐት ደርሷል ። እነ ዩሲን ሰላም ብላቸው ወደ ውጪ ወጣን።
<<ስሚማ!ያ ልጅ>>በእጇ ወደ አንድ ተማሪ እየጠቆመች።
<<የቱ?>> ኢክሩ ወደምታሣየኝ አቅጣጫ ሣይ የተባለው ልጅም ፊቱን አዞረ።
<<እንዴ ማሂር ራሱ እኮ ነው የሚመስለው አየሽው? ኢብቲ ከኃላው፣ ጸጉሩ፣ቁመቱ፣ አረ ሁሉ ነገሩ እንጂ... ከምንም በላይ አረማመዱ ኮፒ ነው የሚመስለው>> ኢክሩ ልክ ናት በጣም ይመሳሰላሉ። ማሂር ማለት እኛ ስድስተኛ ክፍል እያለን እሱ ሰባትኛ ክፍል ተማሪ ነበር። ከሰው ጋር ብዙም አይግባብም፤ ከእኛ ጋር እንዴት እንደተግባባ ባይገባኝም በጣም ፈታ ያለ ልጅ ነበር። ምሣ ሰዐት እሱ እስኪመጣ ጠብቀን ነበር የምንበላው። እኔ እሩዝ ኢክሩ ደግሞ ፍርፍር የያዝን ቀንማ አያስነካንም! ጥርግ አርጎ ነበር የሚበላው። በቃ ልክ እንደ ታላቅ ወንድማችን ነበር የምናከብረው።
<<ስሙ ማን ነው ?>> ኢክሩቲ ከትዝታው መርከብ መለሰችኝ።
<<እንጃ ግን ሎጋው ሲሉት ነበር>> የቅድሙ ትዝ ብሎኝ።
<<ወንድም እንደሌለው ባይነግረንማ ወንድሙ ወይ መንትያው እንል ነበር>> ኢክሩ በጣም ተገርማ ታወራኛለች በመሃል እነዩስራ መጡ ና ወሬ ቀየርን።
*
ዛሬ በጠዋት ነበር ወደ ትምህርት ቤት የደረስነው። ራቢያ ሰፈሯ ከእኛ ስለሚርቅ እኛ ጋር ስትመጣ ነው የምንሄደው። እኔና ዩስራ አንድ ሰፈር ነን፤ ከኢክራም ጋር ደግሞ አቅጣጫችን ሁላ አይገናኝም። የኛ ማርፈድም ሆነ በጊዜ መሄዳችን በራቢያ ይወሰናል፤ ያው እሷ በመጣች ሰዐት እንጂ አንወጣም። ካረፈደች ወደ'ሷ መንገድ እየሄድን እናገኛታለን፤ ዛሬ ቶሎ ስለመጣች በጊዜ ደረስን። ሰልፍ እየተጀመረ ነበር እያስጠላንም ቢሆን ተሰልፈን አለቀ፤ ግን የራሣችንን ወሬ ስናወራ ምን እንደተባለ ሁላ አልሰማንም። ክፍል ስንገባ አቴዳንስ መጠራት ተጀመረ፤ ሲጨርስ ያልተጠራ እጁን ያውጣ ሲባል ከሚያወጡት መሃል እኔም ነበሩኩ። ወደ ቢሮ ሄደን እንድናነጋግር ነገረችን ያረፈዱትንም <ከእሱ ጋር ሂዱ> አለቻቸው። ግር ብለው ወደ ቢሮ ገብተው እያስተካከሉ መውጣት ጀመሩ። እኔ ደግሞ እስኪቀንሱ ብዬ በሩ ጋር ቆሜ ነበር። ወደ ውስጥ ስገባ ከአንድ ልጅ ውጪ ሁሉም ወጥተው ነበር እሱም እንደኔ አዲስ መሰለኝ ሌሎች ለሁለት ለሶስት ነበሩ፤ እኛ ብቻ ስንቀር እሱ ጨርሶ የኔ ተራ ጋር ደረሰ።
<<ማን ነበር ያንቺ ? የአረብ ስም መሆን አለበት እንጂማ ሰሚራ ቢሆን አይጠፍም ነበር..>> ስራውን ቀለል አድርጎ የሚሰራ ይመስላል። ብቻውን ከማሽኖች ጋር እየዋለ በአገኘው አጋጣሚ ለማውራት ይፈልጋል።
<<ኧረ ኤርሚያስ ፒስ ነው>>
<<እንዴ የሰፈሬ ልጅ አቤላ ምነው ፈለከኝ እንዴ?>>
<<እስቲ የዚህን ልጅ ስም ፈልግልኝ>>
<<ኧረ የሰፈር ልጅ ብዬ ሙስና አልሰራም፤ እሷን ላስቀድማት ጠብቁኝ..>>
<<አይ ችግር የለውም>> ሁለቱንም አፈራርቄ አየኋቸው፤ የቸኮሉ ይመስላሉ።
<<የክላስ ልጅ ናት ጣጣ የለውም>> አቤላ እኔን እያየ <<ሎጋው ብለህ ፈልግና ካላገኘኸው ወደ ኦርጅናል ስሙ እንሄዳለን>>
<<አታዝግ ባክህ ስራ ላይ ነኝ>> ኤርሚያስ ነበር ኪቦርዱን እየነካካ።
<<እ.. እሱን ዝም በለው ክላስ መግባት አይፈልግም ማሂር አህመድ እይልኝ>>
<<ምን? እ..ን..ዴ ማሂ...ር>> ሶስቱም አፈጠጡብኝ። ኦህ ደንግጭ ምን እንዳልኩ ራሱ ረሣውት ማሂር ዝም ብሎ ያየኛል፤ አየውና አይኔን ሰበር አደርገዋለሁ።
አቤላ እና ኤርሚያስ እያፈራረቁ ያዩናል። ወደ ራሴ ስመለስ <<ይቅርታ የኔን ስም እየው ...>> ተደናበርኩ።
<<እሺ ማን? አልሽኝ>>
<<ኢብቲሣም ማህሙድ>>
<<ኢንቲሣር?>> አለመሳሳቱን ለማረጋገጥ ያልኩትን አሳስቶ እየደገመልኝ።
<<ኧረ ኢብቲሣም ነው ያለችህ>> ማሂር ነበር። ግን ወዲያው ዝም አለ ፤ወይ ጉዴ ተወዛግቤ አወዛገብኩት።
<<እሺ የሁለታችሁም ተስተካክሏል መሄድ ትችላላችሁ። ግን አትጥፉ ጎራ በሉ..>> ኤርሚያስ ፈገግ እያለ። እኔ እስክወጣ ጨንቆኝ ነበር እየፈጠንኩ መራመድ ጀመርኩ..በሩ ጋር ደርሼ እስካንኳኳ እነማሂር ደረሱብኝና እኩል ወደ ክፍል ገባን። ተማሪው ጢቅ ብሏል። ቦታዬ ላይ አንድ ልጅ ተቀምጦል። ወደ ፊት ጋር ባዶ ወንበር አግኘሁ፤ ሸግን አስተማሪዋ መጸሃፍ ያልያዛቹ ውጡ እያለች ነው። ዩስራ ይዛ ነበር ልጁም ላለመውጣት ብሎ ነው በኔ ቦታ የተቀመጠው። በአይኔ መጸሃፍ ያለበት ቦታ ስፈልግ ማሂርን አይሁት ወደኔ ሊዞር ሲል ቀድሜ ዞሬ ተቀመጥኩ። አስተማሪዋ ወደኔ እየመጣች ነው አንገቴን ደፍቼ አይኖቼን ወደ ደብተሬ አሸሸዃቸው። መድረሷ አልቀረም፤ ከፊቴ ቆሟ በትላልቅ አይኖቿ በቁጣ አፈጠጠችብኝ። በጣም ፈራኻት፤ ገና ከመግባቴ ነገራቶች እየተደራረቡብኝ ነው። ከአስተማሪ ጋር ተግባብቼ መማር የለመድኩ ልጅ አሁን ግን ወደ ጭቅጭቅ እያመራሁ ነው
<<ኧረ ተጠጋልኝ አንተ ስትቀመጥ እረሣኸኛ እኮ!>> አቤላ ነበር። ማሂር ወደ እኔ ተጠጋለትና ተቀመጠ። ምንም መናገር አልቻልኩም እንዴት መጥቶ ሲቀመጥ አላየሁትም ግራ ተጋባሁ ዝም አልኩኝ።
<<ደበረሽ እንሂድ እንዴ?>> አቤላ ዝም ስል እነሱ ስለተቀመጡ መስሎታል።
<<ኧረ አልደበረኝም.. እ.. እንዴት መጣችሁ?>>
<<ቲቸር ሃይለኛ ናት! መጻሃፍ ካልያሽ ደግሞ ያልቅልሻል። ወደ አንቺ ስትመጣ እንቅደማት ብለን ነበር። እሷም መፅሃፉን ስታይ አስቀየሰች፤ ምትጋተተው ተማሪ እየፈለገች ነው።>> ፈገግ አለ፤ አቤላ። ደግሞ ጨዋታ አያልቅበትም በቃ ማሣቅ ሙዱ ነው።
<<ኧረ እናንተ የሌለ ተመቻችታቹ የለ..>> ሶስታችንም ቀና ስንል ባቢ ነበር። ሰላም ከተባባሉ ቡኃላ እጁን ሲዘረጋ <ይለፈኝ> አልኩት ሶስቱም አዩኝ። ባቢ ንቄው መስሎታል መሰለኝ ፈታ ብሎ ማውራት አልቻለም። አቤላ ያወራል እኛ እንስቃለን። <<ባቢ እእ ምንድነው ጓደኞችክ ጓደኛችንን ይዘው አንለቅ ያሉት?>>
<<እሰይ ዪሣ ተባረኪልኝ እሱን ለመጠቅ ነው የኔም አመጣጥ። ቅድም የት ነበራቹ?>> ራቢያ ኮስተር ለማለት እየሞከረች።
<<መጀመሪያ አንቺ መልሺልኝ።>> እኔ ላይ ጣቷን እየቀሰረች። ለነገር እንደሆነ እኔም አልጠፋኝም። ትንሽ ላድርቃቸው በሚል <<ማሂር የት ነበርን?>> ብዬ ስመለከታቸው እርስ በእርስ ይተያያሉ። ማሂር ለመናገር ጉሮሮውን ሲጠራርግ
አቤላ ፈጠን ብሎ
<<አትቸገር ወንድሜ እኔ ላስረዳቸው። ያው ለትንሽ ጉዳይ ወደ ቢሮ አቅንተን ነበር እሷን ስንጨርስ ወክ አደርገን ወደ ክፍል መጣን። ግን እወቁልኝ እኔ አጃቢ ነበርኩ ሃሃሃሃሃ...>> ሁሉም ሣቀ።
<<አንተ የተመታህ..>> ብሎ ማሂር ሲነሳ አቤላ እየሮጠ ወጣ።
.
.
ይቀጥላል...

www.tgoop.com/Habibacalligraphy

tgoop.com/Habibacalligraphy/1934
Create:
Last Update:

BY Habiba Calligraphy

Share with your friend now:
tgoop.com/Habibacalligraphy/1934

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Telegram iOS app: In the “Chats” tab, click the new message icon in the right upper corner. Select “New Channel.” Read now Select “New Channel” Members can post their voice notes of themselves screaming. Interestingly, the group doesn’t allow to post anything else which might lead to an instant ban. As of now, there are more than 330 members in the group. More>>
from us

Telegram Habiba Calligraphy
FROM American