tgoop.com/Hijramuslim/1442
Create:
Last Update:
Last Update:
ወዳጄ ራስህን እይ
ምን ላይ ቆመሀል,,ምንስ ይዘሀል,በምን እየኖርክ ነው,,ከማን ጋር ነህ ወዳጄ ራስህን እይ::አጠገብህ ያሉ ሰዎች ከ አንተ ርቀው ራሳቸውን በተሻለ ነገር ሲያደርሱ ከአንተ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሲቆሙ; የተሻለ ኑሮ ሲኖሩ ከ አንተ ተሽለው ሲገኙ. ያኔ ራስህን እይ ያኔ ራስህን ፈትሽ : አብረውክ እየዋሉ አዳሩን ራሳቸውን ለመለወጥ እንደማይሮጡ በምንታውቃለህ ለሊቱን ከአንተ ጋር ሲያባክኑ ሲለይዩክ ራሳቸውን ስላልመቀየራቸው ምን ዋስትና አለህ:: ራስህን ሸውደካል ያኔ ራስህን አታለሃል
ወዳጄ ራስህን እይ ራስህን ፈትሽ ምን ላይ ቆመሀል ምንስ ይዘሀል ስንት አመት ምን እንዳለህ በምን እይኖርክ እንዳለህ ሳታውቅ አለፈ::ስንት አመት ወዳጆችህ እየተለውጡ እያደጉ እያየህ ስታጨበጭብ ኖርክ: ስንት ጊዜ ጥያቄዎችህን ሳትፈታ ኖርክ.......ጀምር..ጀምር እስቲ ጀምር መኖርን መስራትን ጀምር ማሰብን ጀምር መለወጥን ጀምር ህይወትን ማስተንተን ጀምር: ወዳጄ ያባከንከውን ጊዜ ተወው ወዳጄ ወደ ፊት እይ ራስህን ጠይቅ,, ራስህን እይ መኖር ስትጀምር ማሰብ ስትጀምር መስራት ስትጀምር ያኔ ራስህን አይተሀል ያኔ መንገድክን አግኝተሃል::ወዳጄ በቻልከው አቅም ራስህን እይ በቻልከው መጠን ራስህን አግኝ::
BY Hijra Tube
Share with your friend now:
tgoop.com/Hijramuslim/1442