tgoop.com/Hijramuslim/1447
Create:
Last Update:
Last Update:
አላህ ካንተ የሚፈልገው እንከን አልባ (ፍፁምነትን) ሳይሆን ወደ እርሱ በሚደረገው ጉዞ ላይ በሙሉ ልብ የርሱ ሆነህ መገኘትህን ነው ያ ደግሞ ስሙ ልህቀት (excelence) ይባላል..ትርጉሙ ደግሞ "አላህ የሰጠህን ጊዜ፣ሀይል እና ፀጋ(ኒዕማ) በአግባቡ መጠቀም መቻልና ለነገሮች ተገቢውን ትኩረት መስጠት ነው"...መገለጫው ደግሞ ነገሮችን በአግባቡ፣ በእርጋታ፣ በተገቢው መንገድ መከወን መቻል ነው ...ብዙዎቻችን በኢማናችን ጠንካራ ፣በምንሰራው ስራ ስኬታማ መሆን እንፈልጋለን ነገር ግን ጊዜያችንን ፣ኋይላችንን እንዲሁም አላህ የሰጠንን ፀጋ በአግባቡ ግን ማዋል አንፈልግም ..ነገራቶችህን በምን ያህል ትጋት እየከወንክ ነው?ጥዋት ስንት ሰአት ነው የምትነሳው? ቀንህስ በምን እያለፈ ነው ? ቁርዓን በቀን ውስጥ ምን ያህል ትቀራለህ ?ቢዝነስህ ፣ት/ት ህ ፣የትዳር ህይወትህን ለማሻሻል ምን እያደረግክ ነው ...ዛሬውን ያልሰራ ማህበረሰብ ስለነገ ምን ብሎ ነው የሚያወራው? ...ነገ ዛሬ በአግባቡ ለተዘጋጁት ትሆናለች አትጠራጠር !
መልካም ጁምዓ ♥
የጅምዓ መልዕክቴ
https://www.facebook.com/fethudin.ali.7 በፌስቡክ ይወዳጁን
BY Hijra Tube
Share with your friend now:
tgoop.com/Hijramuslim/1447