tgoop.com/Hulaadiss/38486
Last Update:
ትራምፕ ለጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ባይደን ምስጋና መዉሰዳቸዉን ተገቢ ያልሆነ ሲሉ ተናገሩ
ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት በእርሳቸውና በመጪው አስተዳደራቸው ግፊት ባይደረግ ኖሮ ፈጽሞ ሊደረስ እንደማይችል በመግለጽ ሙሉ እውቅና ሰጥተዋል።"በዚህ ስምምነት ውስጥ ባንሳተፍ ኖሮ የተኩስ አቁም ስምምነቱ በጭራሽ አይደረስም ነበር" ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል ሲል የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
"መንገዱን ቀይረነዋል፣ እናም በፍጥነት ቀይረነዋል፣ እውነቱን ለመናገር፣ እኔ ስልጣን ላይ ከመሆኔ በፊት ቢደረግ ይሻላል" ብለዋል።ትራምፕ በቴሌቭዥን ቀርበው አስተያየት የሰጡ ሲሆን ባይደን "ምንም አላደረጉም!" ሲሉ ተናግረዋል።"ይህን ባላደርግ ኖሮ ታጋቾቹ በጭራሽ አይወጡም ነበር" ሲሉም አክለዋል። በሌላ በኩል የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት ላይ መደረሱን አረጋግጧል፡፡
የቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት የእስራኤል ተደራዳሪ ቡድን ስምምነቱ መጠናቀቁን አረጋግጧል።የሀገሪቱ የደህንነት ካቢኔ እና ከዚያም መንግስት ስምምነቱን ለማፅደቅ ስብሰባ ይቀመጣል፡፡ስምምነቱን የሚቃወሙት ሁለት የቀኝ ክንፍ ሚኒስትሮች ኢታማር ቤን ጊቪር እና ቤዛሌል ስሞትሪች በተቃውሞ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ተናግረዋል።
የተኩስ አቁም እና የታጋቾች የመልቀቅ ድርድር ምዕራፍ አንድ ሲያበቃ፣ መንግስትን ለማውረድ ተቃዉሞ ኃይሉን እንደማይቀላቀሉ ጠቁመዋል።የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ አንቶኒ ብሊንከን የመጀመሪያዎቹን ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾች በመልቀቅ የተኩስ አቁም ስምምነቱ በታቀደው መሰረት እሁድ ይጀመራል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
BY Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Share with your friend now:
tgoop.com/Hulaadiss/38486