tgoop.com/Hulaadiss/38576
Create:
Last Update:
Last Update:
#CapitalNews ከዩ.ኤስ.ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሃብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን እንዳያስተላልፉ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ
በአሁኑ ወቅት ከዩ.ኤስ.ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ድርጅቶች በማናቸውም መልኩ ሃብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑንና ይህነ በሚተላለፉ ተቋማት ላይ እርምጃ እወዳለሁ ብሏል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በጻፈው እና ለካፒታል በደሰረዉ ደብዳቤ ላይ እንደተገለፀዉ ያለ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግልፅ ፍቃድ ንብረት የማስተላለፍ፣ የማስወገድ ወይም የመሸጥ ወይም ከመደበኛ/ፕሮጀክት ስራዎች ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ጠይቋል።
ይሁን እንጂ በማናቸውም መልኩ ሃብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑን የገለፀው ባለስልጣኑ ይህንን ማሳሰቢያ በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ጠቁሟል።
ከሰሞኑ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) በኩል የእርዳታ ማቆም ውሳኔ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንና ዝርዝር ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል የሚያከናዎን መሆኑን ተቆጣጣሪ አካሉ አስታውቋል ።
BY Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/cRxp0mYE9bOcSQoXn4p48BvbunhyHfApRvKT4jff1pxuX_7uBkZ5xj_g6FMzRDEEAwSnQ1rj8ymokRrDI0Sx-aWnfKn8jKByrHxXyKP86L7IkC8IWuYVDSPQR0STPoukA6fdTWKGIw2qfw0BeKo4fsuroFDx79xa6Z2P5tNuf5Y9a5nE_9JPY6H-t872SOGv6cCZyySj76dEZ-YKRTuSOrr2B3vuP8-c1VLm4D2HNqk9zUWLS_A8KFegvtDhfUGkXRDkfn_L6J4MAT3-YjY0-2NeRKtN6zUIjFRC379Leah2S-5aYKQzhBXjWgxz_wfiiQvkghn6lZgXjZmSbSiS-Q.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/Hulaadiss/38576