tgoop.com/IbnShifa/4715
Last Update:
የቢድዐህ ባለ ቤቶችን መለያየት አይክበዳችሁ!!
———
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ አውስተው እንዲህ አሉ:-
{احْشُرُوا الَّذِينَ ظَلَمُوا وَأَزْوَاجَهُمْ} الصافات ٢٢
«እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ሰብስቡ፡፡” በተባለ ቀን ጓደኛ ከመሆን በአላህ ይሁንብኝ በዚህ ሀገር የቢድዐህ እና የስሜት ባለ ቤቶችን መለያየት ቀላል ነው።» [አል-ካፊየቱ ሻፊያ…]
ኢማሙ'ል አል-ባኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“በብቸኝነት ምንም አይነት ግኑኙነትና የሚያሰባስብ ነገር የሌለን ሆነን መሞት ለኛ የተሻለ ነው በአንዲት ነጥብ አላህንና መልክተኛውን ከምናምፅ። ለእኛ በጥመት ከመሰባሰብ ቁርኣንና ሀዲስን በመፃረር ላይ በሚያዘጋጁት መንገድ፣ ሸሪዓውን የሚፃረር መሆኑን እያወቁ ከትእዛዙ ብዙውን እያመፁ ከእነሱ ጋር ከመሰባሰብ ብቸኝነት በላጭ ነው።” [ሲል ሲለቱል ሁዳ ወንኑር]
የየመኑ ሙሀዲስ በመባል የሚታወቁት ሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሓዲ'ል ዋዲዒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“ሠለፊይ የሆነ ሰው: የተሰጠውንም ያህል (ጥቅምና ገንዘብ) ቢሰጠው ሱናን፣ ደዕዋን አይሸጥም! እሷ ከገንዘብም ከዝምድናም ከሁሉም ነገር በላጭ ናት!!።” [አል ኢማም አል'መዒይ 253]
ስንቱ ነው "አገሌኮ የረጅም ጊዜ ጓደኛዬ ነው፣ አገሌማ ቤተሰብ ስለሆነ ነው፣ አገሌማ ወደ ሱንና ለመምጣት ሰበብ ሆኖኛል…" እያለ በጭፍን ወደ ቢድዐህ እና ጥመት የሰመጠው?! ወደ ሱንና እንድትመጣ ሰበብ ቢሆንህም ሱንናን ከተወ እሱን ትተህ ሱናን አጥብቀህ መያዝ ነው!፣ ይህ ጓደኝነትና ቤተሰባዊነትም ከሐቅ ከተቀደመ ነገ አላህ ፊት ያዋርዳል!! ሐቅ ከሁሉም በፊት ቀዳሚ ነው!! ፈፅሞ ከሐቅ ጋር የሚወዳደር ነገር የለም!!
በዚህ ወቅት ስንቱ ነው ሱናን ለገንዘብ፣ለክብርና ለዱኒያ ጥቅማጥቅም ሽጦ ትላንት ያውቀው የነበረውን ሐቅ መልሶ ሲተች፣ ትላንት ያወግዘው የነበረውን ባጢል መልሶ ሲያደንቅና እውቅና ሲሰጠው የሚስተዋለው!! ትክክለኛ ጥመት ማለት ይህ ነው!!
አላህ በሐቅ ላይ ፀንተው ከሚገናኙት ባሪያዎቹ ያድርገን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (www.tgoop.com/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
BY [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
Share with your friend now:
tgoop.com/IbnShifa/4715